Ethiopia

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር በተጠናቀቀው በጀት አመት 10 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ለፀ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከሰጠው ብድር በተጠናቀቀው በጀት አመት 10 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ለፀ።ባንኩ የትግራይ ክልል ፕሮጀክቶችን ሳይጨምር የተበላሸ ብድር ደረጃውን ወደ 17 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን አስታውቋል። የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በትግራይ ክልል ያሉ በርካታ ፕሮጀክቶች ወደ ተበላሸ ብድር መግባታቸው አመቱን ለባንኩ ፈታኝ አድርጎታል ብለዋል።


 የገጠመውን ችግር ለማካከስ ባንኩ ፈጣን ለውጦችን በማድረጉ ትግራይን ሳይጨምር በ2013 ዓ.ም የነበረውን የተበላሸ የብድር መጠን ከ15 ቢሊዮን ወደ 9 ቢሊዮን ብር ዝቅ ማድረግ ችሏል ነው ያሉት። በዚህ የማስተካከያ እርምጃም ባንኩ ወደ 11 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከብድር መሰብሰቡንና በበጀት ዓመቱ 3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ማትረፉንም ገልፀዋል።ኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር አሰባሰብ ላይ የጀመረውን ስራ በማጠናከር በ2015 በጀት አመት 14 ቢሊዮን ብር ከብድር ለመሰብሰብ ማቀዱን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button