Politics

ለአሜሪካ ጦር መሳሪያዎች በጠላት እጅ መገኘት ተጠያቂዋ ሳውዲ ናት ተባለ::

ለአሜሪካ ጦር መሳሪያዎች በጠላት እጅ መገኘት ተጠያቂዋ ሳውዲ ናት ተባለ

ሳውዲ መራሹ ጦር ታጥቋቸው የነበሩ አሜሪካ ሰራሽ ጦር መሳሪያዎች ለሶስተኛ ወገን ተላልፈው መገኘታቸው ዋሽንግተንን አስደንግጧል፡፡

መሳሪያዎቹ በየመን በሚገኙ ሁቲዎች እና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ባላቸው ቡድኖች እጅ ታይተዋል ተብሏል፡፡

ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው አሜሪካ ለወዳጇ ሳውዲ አረቢያ የሸጠቻቸው መሳሪያዎች በጠላት እጂ መገኘታቸው የሁለቱን ሀገራት ወዳጂነት አደጋ ላይ ይጥዋል የሚል ስጋትን ፈጥሯል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ሳውዲ መራሹ ጦር ከአሜሪካ የገዛውን ጦር መሳሪያ ለሶሶተኛ ወገን አሳልፎ ለመስጠት የሚያስችለውን ህግ እና  ደንብ ተላልፏል በመባሉ ነው፡፡

ሲ ኤን ኤን  ሚስጥሩን ከደረሰበት እና ለህዝብ ይፋ ካደረገው በኋላ የአሜሪካ የመከላለከያ ሀላፊዎች ነገሩ እውነት መሆኑን አምነው ተቀብለውታል፡፡

ፔንታጎን መሳሪያዎቹ  በማን በኩል ለጠላት ወታደሮች ተላልፈው እንደተሰጡ ለማጣራት ምርመራየን ጀምሬያለሁ የሚል መግለጫም ሰጥቷል፡፡

አሜሪካ በተለያዩ የግጭት ቀጠናዎች የተሰማሩ ወታደሮቿች እራሷ በሰራችው መሳሪያ ከአሸባሪ ቡድኖች ጥቃት እንዳይደርስባቸው ስጋት ወስጥ  ገብታለች፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button