EthiopiaRegions

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሕጋዊ እርምጃዎች ተወሰዱ።

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የሕግ የበላይነት ለማስከበር ሕጋዊ እርምጃዎች ተወሰዱ።

ሱሉልታ

በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሻሸመኔ

ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ቡራዩ

የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት ሲጠይቅ የነበረ፣ ቲተር: ማዕተምና የመታወቂያ ወረቀት በቄሮ ስም አዘጋጅቶ በመሸጥ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ለገጣፎ ለገዳዲ

በቄሮ ስም የ62 ወጣቶችን ፎቶ በማሰባሰብና ወረቀት ላይ በመለጠፍ የቄሮ አደረጃጀት ከቀበሌ እስከ ላይ መኖር አለበት በሚል ወጣቶችን ሲያታልሉና ሲያደረጁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ጅማ

በሕገ ወጥ ስራ ላይ ተሰማርተው ሕገ ወጥ ግንባታ ሲያካሄዱ የነበሩ 42 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰዎች ላይ ሙሉ መረጃ ተሰባስቦ ለሕግ ሊቀርቡ ነው፡፡
ድንገት በተደረገው ፍተሻም 2ሽጉጥና 180 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

አዳማ

በቅርቡ በከተማው ለተከሰተው ግጭት መነሻ በመሆን ሰዎችን ሲያነሳሱ የነበሩና ግጭቱ የብሔር መልክ እንዲይዝ አድርገዋል የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሞጆ

ጨለማን ተገን በማድረግ ፋብሪካን ለመዝረፍ ሲንቀሳቁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በአንደኛው ግለሰብ እጅ ሽጉጥ ተይዟል፡፡

ሰበታ

በሕገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሰማሩ፣ ምግብ ቤት ገብተው በመመገብ ሒሳብ የማይከፍሉና ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button