SportSports

በኮፓ ኢጣሊያ ኤስ ሚላን ናፖሊን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተቀላቅሏል

በኮፓ ኢጣሊያ ኤስ ሚላን ናፖሊን በማሸነፍ ወደ ግማሽ ፍፃሜ ውድድር ተቀላቅሏል

ትናንት ምሽት ጁሴ ሜዛ ላይ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ያከናወኑት ኤስ ሚላን እና ናፖሊ በሮዘነሪዎቹ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡

የጎንዛሎ ሂግዌን ምትክ በመሆን ባለፈው ሳምንት በ30 ሚሊየን ፓንድ ሂሳብ ከጅንዋ ሚላንን የተቀላቀለው ክሪዚስቶፍ ፒያቴክ የጨዋታው የመጀመሪያ 30 ደቂቃዎች ውስጥ ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች ደግሞ ቡድኑን ወደ ግማሽ ፍፃሜ እንዲሻገር አስችሏል፡፡

ፖላንዳዊው ተጫዋች የመጀመሪያ ጨዋታውን በሴሪ ኤው ተቀይሮ በመግባት ያከናወነ ሲሆን በትናንት ምሽቱ ጨዋታ ቡድኑን ወደ ድል ጎዳና በመውሰድ  የወጣበትን ዋጋ እየመነዘረ ይገኛል፡፡

ኤስ ሚላን ለተከታታይ ሶስተኛ ጊዜ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፍ የቻለ ሲሆን ነገ ምሽት የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያቸውን ሳንሴሮ ላይ ከሚያደርጉት ኢንተር ሚላን እና ላትሲዮ አሸናፊ ጋር ይገናኛል፡፡

ዛሬ ምሽት ፊዮረንቲና በስታዲዮ አርቴሚዮ ፍራንቺ ሮማን ሲያስተናግድ፤ ዩቬንቱስ ወደ ቤርጋሞ አቅንቶ በስታዲዮ አትሌቲ አዙሪ ደ ኢታሊያ አታላንታ ቤርጋሞን ምሽት 4፡45 ላይ ይገጥማል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button