Ethiopia

ህወሓትን ሲደግፉ የነበሩ ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ ከኢንተርፖል ጋር እየሰራን ነዉ-ፌደራል ፖሊስ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣2013  ለአሸባሪው ህወሓት የኢኮኖሚ ምንጭ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩ 117 የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያ ቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ህገወጥ ምንዛሪን አስመልክቶ ለአርትስ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ባካሄደው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ለሽብር ቡድኑ የኢኮኖሚ ምንጭ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች እና መኖሪያቤቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ የአሸባሪው ቡድን የፋይናንስ ምንጭ እንዲደርቅ የሚያደርጉ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡

ቡድኑ ከፍተኛ የኑሮ ውድንት እንዲፈጠር በማድረግ ህዝብ በመንግስት ላይ እንዲማረር የተቻላቸውን ሁሉ እየሰሩ መሆናቸውን እንደደረሰበት ገልጿል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የአሸባሪው ቡድን ከፍተኛ የገቢ ወይም የፋይናንስ ምንጭ በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት የዘረጋቸው ኔትወርኮች መሆናቸውን ጠቁሞ ፤ በተለይ ዶላርን በጥቁር ገበያ በውድ ዋጋ በመሰብሰብ እና የኋላ አገልግሎትን በመጠቀም እንደሆነ
ገልጿል፡፡

በህገወጥ ተግባሩ በሚያጋብሰው ገቢም የጦር መሳሪያ ግዥን በመፈጸም ለጥፋት ተልዕኮው እንደሚጠቀምብት የጠቆመው ኮሚሽኑ ፤የፌደራል ፖሊስና የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገርም ባካሄዱት ረጅም ጊዜ የፈጀ ጥናት ፤በተደረገ ምርመራና ክትትል የደረሰባቸውን ተቋማት ይፋ አድርጓል፡፡ በህገ ወጥ ተግባሩ በሚያጋብሰው ገቢም የጦር መሳሪያ ግዥን በመፈፀም ለጥፋት ተልዕኮው እንደሚ ጠቀምበት የጠቆመው የኮሚሽኑ መግለጫ፤ ፌዴራል ፖሊስና የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል በሀገር ውስጥና በውጭ ሃገርም ባካሄዱት ረጅም ጊዜ የፈጀ ጥናትና  በተደረገ ምርመራና ክትትል የደረሰባቸውን ተቋማት ይፋ አድርጋል።

በጥናቱም ኔትዎርኮቹን የመለየት ስራ የተከናወነ ሲሆን በኔትዎርኮቹ ውስጥ የተካተቱ ድርጅቶችና ግለሰቦች መለየቱን እና ለህግ ለማቅረብ ከአለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ጋር በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ አረጋግጧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button