Ethiopia

የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሊጀምሩ ነው::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሊጀምሩ ነው::ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ከነገ ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃንማድረግ እንደሚችሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምረጡኝ ዘመቻቸው የሚጠቀሙበት ነፃ የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ እጣ ድልድል መርሐ-ግብር ተከናውኗል፡፡
ድልድሉ 25 በመቶ ለፓርቲዎች በእኩል ክፍፍል የሚሰጥ ሲሆን፣ በስራ ላይ ባሉ የፌዴራልና የክልል ምክር ቤት ወንበር 5 በመቶ፣ በእጩ ብዛት 40 በመቶ፣ በሴት እጩ 20 በመቶ፣ በአካል ጉዳተኛ እጩ ብዛት 10 በመቶ መሰረት በማድረግ ድልድል ተደርጓል ተብሏል። ድልድሉ ለ46 የፖለቲካ ፓርቲዎች በ21 ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በ23 ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዲሁም በ8 ጋዜጦች በጠቅላላው በ52 መገናኛ ብዙሃን የሚከናወን ነው ተብሏል።
በሬዲዮ 620 ሰዓታት፣ በቴሌቪዥን 425 ሰዓታት እና በጋዜጣ በ625 አምዶችን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ለምርጫ ቅስቀሳቸው ይጠቀማሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የእጣ ድልድሉ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና ብሮድካስት ባለሥልጣን በጋራ በተዘጋጀ መድረክ የተከናወነ ሲሆን በዚህም ፓርቲዎች በተደለደለላቸው እጣ መሠረት ከመጋቢት 30 እስከ ግንቦት 23 በመገናኛ ብዙኃን ነፃ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button