አሁንም በአፍሪካ ምድር በምርጫ ማግስት ሰው ይገደላል፡፡ በዚምባቡዌ የተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤቱ ለሰው ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡
የፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነው በምርጫው የቀረቡት ኔልሰን ቻሚሳ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ አሸናፊ ሆኗል መባሉን ባለመቀበላቸው ደጋፊዎቻቸው ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ ወጥተዋል፡፡
የምናንጋግዋ ወታደሮችም ሰልፈኞቹ ላይ ተኩሰዋል፡፡ እስካሁን 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቋል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ መገናኛ ብዙሀን ቁጥሩን አምስት ያደርሱታል፡፡
የኬንያው ደይሊ ኔሽን እንደዘገበው የቀድሞ ቅኝ ግዛቷ ጉዳይ እንዳሳሰባት የገለጸችው እንግሊዝ የሀገሪቱን ባለስልጣናት ነገር አብርዱ እያለች ነው፡፡