World

የመን አዲስ የፖሊዮ ክትባት ጀመረች፡፡

የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ የክትባት ዘመቻዉ እየተካሄደ ያለዉ ከአለም አቀፉ የጤና ድርጅት፣ ከዩኒሴፍ እና ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነዉ፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበዉ በክትባት ዘመቻዉ ከ5 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ይከተባሉ፡፡
ክትባቱ ከ5 አመት በታች ላሉ ህጻናት እንደሚሰጥና ከአሁን በፊት የተከተቡ ህጻናትንም ጭምር እንደሚያካትት ታዉቋል፡፡
በሀገሪቱ ያለዉ የእርስ በእርስ ጦርነት በህጻናት ላይ እያስከተለ ያለዉ ችግር የከፋ መሆኑን የገለጸዉ ሚንስቴሩ ፤ በተቻለ መጠን ህጻናቱን በያሉበት በመድረስ ክትባቱን እንደሚሰጥ አስታዉቋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button