loading
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዩስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጎበኙዋቸው፡፡

በጉብኝቱ ላይ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል ተገኝተዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩም እንዳሉት አቡነ መርቆርዮስን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን በመጎብኘታቸው ከፍ ያለ ደስታ እንደተሰማቸው ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ከአቡነ መርቆርዮስ ጋር ስለይቅርባይነትና ስለፍቅር ተወያይተዋል፡፡

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ጠቅላይ ሚኒስተሩ አቡነ መርቆርዮስን መኖሪያ ቤታቸው ድረስ ተገኝተው በመጎብኘታቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ባለፉት 26 ዓመታት ለሁለት ተከፍለው የሀገር ቤትና የውጭ ሲኖዶስ እየተባሉ ሲጠሩ የነበሩት ሁለቱ ሲኖዶሶች ቃለ ውግዘታቸውን አንስተው ወደ ዕርቅ መምጣታቸው ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ብፁአን አባቶች ከአስር ቀናት በፊት ነበር ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመሆን አዲስ አበባ የገቡት፡፡

ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *