
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ እንደገለፁት ኮሚቴው በስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ በዚህም መሠረት፦
1. የአገር ውስጥ የግል ባንኮች ከብሄራዊ ባንክ ለሚገዙት “27% ቦንድ” ብሄራዊ ባንክ የሚከፍላቸው ወለድ አሁን ካለው ከ3% ወደ 5% ከፍ እንዲል፣
2. የኢትዮጵያ ዳያስፖራ በአገር ውስጥ ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚያስቀምጡት የ50,000 የአሜሪካን ዶላር ገደብ እንዲነሳ፣
3. የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ግኝታቸውን 30% ለብሄራዊ ባንክ የሚሸጡበት ተመን በመግዢያና በመሸጫ መካከል ባለ (አማካይ) ዋጋ እንዲሆን፣
4. በውጭ ምንዛሪ ክፍያ እንዲቀበሉ የተፈቀደላቸው የንግድ ድርጅቶች በስራ ላይ ካለው ዝርዝር በተጨማሪ:-
* በኤርፖርት ውስጥ የሚሰጥ የቴሌኮም አገልግሎት፣
* ለውጭ ቱሪስቶች የቻርተርድ አገልግሎት የሚሰጡ የግል አየር መንገዶች፣
* የውጭ ዜጎችን የሚያስተናግዱ የእንግዳ ማረፊያዎች፣
* የውጭ ዜጎችን የሚያስተናግዱ ልዩ ክሊኒኮች እና
* የውጭ ዜጎችን የሚያስተናግዱ ሆስፒታሎችን እንዲጨምር ኮሚቴው መወሰኑንም አቶ ፍፁም ተናግረዋል።
ኤፍ ቢ ሲ
አርትስ 24/12/2010