AfricaEthiopiaPolitics

ሳልቫ ኬርና ሪክ ማቻር የህዝብ አደራ አለባችሁ ተብለዋል

አርትስ 03/01/2011
የተባበሩት መንግስታት ዲፕሎማቶችና የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሪዎቸ የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች መሪዎች የተፈረመውን የሰላም ስምምነት እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዝዳት ሳልቫ ኪር እና ተቀናቃኛቸው ዶክተር ሪክ ማቻር በኢጋድ አደራዳሪነት አዲስ አበባ ላይ የፈረሙትን ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ህዝባቸውን እንዲክሱ ነው መሪዎቹ የጠየቁት፡፡

ኒውስ ናው አውንደዘገበው የኢጋድ ሊቀመንበር ዶክተር አብይ አህመድ ይህ ስምምነት ተጥሶ ዳግም የአንድም ሰው ህይወት አደጋ ላይ መውደቅ የለበትም ብለዋቸዋል፡፡

በስምምነቱ ላይ የተገኙት የተለያዩ ሀገራት ባለስልጣናትም ከእንግዲህ በደቡብ ሱዳን ደም አፋሳሽ ግጭት መቆም አለበት ፤ይህ የሚሆነው ደግሞ እናነተ ቃላችሁን ስትጠብቁ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button