Tourism

በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል 15 ሺህ ቱሪስቶች ይታደሙታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

በጎንደር የሚከበረውን የጥምቀት በዓል 15 ሺህ ቱሪስቶች ይታደሙታል ተብሎ እየተጠበቀ ነው

በነገው ዕለት በጎንደር ከተማ በድምቀት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ለመታደም ከተለያዩ ሃገራት የመጡ 15 ሺህ አገር ጎብኚዎች እንደሚታደሙበት ተገልጿል።

ይህንን እና በክልሉ ሌሎች አካባቢዎች የሚካሄዱ የበዓሉን አከባበሮች ከጸጥታ ችግር የጸዳ ለማድረግ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቅቆ ወደስራ መግባቱንም የክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀው በክልሉ በዋናነትም በጎንደር የሚካሄደው የበዓሉ አከባበር ልዩ ጥበቃ ይደረግለታል።

የፖሊስ ኮሚሽኑ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ አህመድ እንዳስታወቁት ፖሊስ የጥምቀት በዓል በአደባባይ የሚከበር በመሆኑ ከተለመደው ጊዜ የተለየ የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገ ነው ብለዋል ።

ጥበቃው በግልጽ እና በስውር የፖሊስ ሃይል እየተካሄደ መሆኑንና በተለይም

የውጭ ሀገራት ጐብኝዎች በሚጓጓዙበትና በሚያርፉበት አካባቢ የተጠናከረ ልዩ ጥበቃ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button