በኢትዮጵያ ከተለያዩ አገራት የመጡ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኞች ይኖራሉ፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኤጄንሲ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ከ900,000 በላይ ስደተኞች እንደሚገኙ ተናግረው ፤ ኢትዮጵያ ለዚህ ውለታዋ ልትመሰገን ይገባል ብለዋል።
ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ በኢትዮጵያ የአራት ቀናት የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን
ከዉጭ ጉዳይ ቃላቀባይ ጽ/ቤት እንዳገኘነዉ መረጃ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያጸደቀችው አዲስ ተራማጅ አዋጅ የስደተኞችን ዘላቂ ህይወት በመለወጥ በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋልም ብለዋል ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ።