loading
የገቢዎች ሚኒስቴር ከሀገር ውስጥ ታክስ 7.5 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ
የገቢዎች ሚኒስቴር ከሀገር ውስጥ ታክስ 7.5 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን ገለፀ
ሚኒስቴሩ የ2011 በጀት ዓመት የጥር ወር የስራ እንቅስቃሴውን ገምግሟል፡፡
በግምገማዉም ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በጥር ወር ከሀገር ውስጥ ታክስ ለመሰብሰበሰ ካቀደው 10.92 ቢሊየን ብር 7.58 ቢሊየን ብር (69.4 %) መሰብሰቡን ሚኒስትሯ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡
እንደ ሚኒስትሯ ገለፃ በአዲስ አበባ የተደረገው የ2009 ዓ.ም የቀን ገቢ ግምት ስረዛ የታክስ ምህረት ነው ብሎ በማሰብ ሳይከፍሉ መዘግየት፡አዳዲስ የታክስ ዉሳኔዎች የተሰጣቸዉ ግብር ከፋዮች ወደ ክፍያ ከመግባት ይልቅ ወደ ክፍያ ስምምነት መምጣት፣ የገቢ ፊሲካል ስራዎች (ኦዲት፣ የእዳ አሰባሰብ፣ የታክስ ቅሬታ አፈታት፣ አፈፃፀም ደካማ መሆን፣ ከቫት ዊዝሆሊዲንግ ጋር ተያይዞ ለኮንስትራክሽን ስራዎች ከመንግስት የክፍያ መዘግየት፣ የስኳር ፋብሪካዎች ለገበያ ያላቸዉ አቅርቦት በመቀነሱ በወሩ ያስገባሉ ተብሎ የታቀደዉ የተጨማሪ እሴት ታክስና የኤክሳይዝ ታክስ አሰባሰብ ላይ ተፅኖ ማሳደሩ በወሩ የግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ ያጋጠሙ ችግሮች ናቸው፡፡
በቀጣይ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ እና የገቢ እቅዱን ለማሳካት ገቢን የሚያግዙ ስራዎችን ለይቶ በፍጥነትና በጥራት መፈፀም፣ የህግ ማስከበር ስራዎችን ይበልጥ ማጠናከር፣ የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር የግብር ከፋዮችን ግንዛቤ ከፍ ማድረግ ፣ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን ማጠናከር እና ሀገራዊ የታክስ ንቅናቄው የፈጠረውን መነቃቃት እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም መሰብሰብ የሚገባው የታክስ ገቢ በትክክል እንዲሰበሰብ እንደሚሰራ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *