loading
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር ጨዋታዎች ነገ ይጀመራል

የ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሁለተኛው ዙር መርሃግብር፤ የ16ኛ ሳምንት ግጥሚያዎች በነገው ዕለት ይጀመራሉ፡፡

ክልል ስታዲየም ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ ላይ ከሃዋሳ ከተማ 9፡00 ላይ ይገናኛሉ፡፡

ዕሁድ ደግሞ በርካታ ጨዋታዎች ሲከናወኑ በክልል ስታዲየሞች የሚደረጉት ሁሉም ግጥሚያዎች በተመሳሳይ ቀን 9፡00 ይደረጋሉ፡፡

ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ደደቢት ከሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ጋር በትግራይ ደርቢ ትግራይ ስታዲየም ላይ ይፋለማሉ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ወደ ባህር ዳር አቅንቶ ከባህር ዳር ከተማ ጋር ግጥሚያውን ያከናውናል፡፡ በአዲስ አሰልጣኝ ሁለተኛውን ዙር የሚጀምረው ኢትዮጵያ ቡና ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያ ተጉዞ ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ይፋለማል፡፡

የጎንደሩ ፋሲል ከነማ የደቡቡን ሲዳማ ቡና ፋሲለደስ ላይ ያስተናግዳል፤ አሰልጣኝ አሸናፊ በቀለን የቀጠረው ወላይታ ድቻ ሶዶ ላይ ከስሑል ሽረ ጋር ይጫወታል፡፡

ጅማ አባጅፋር ከአዳማ ከተማ ጅማ ላይ ግጥሚያቸውን ይከናወናሉ፡፡

የስዩም ከበደው መከላከያ ከ ደቡብ ፖሊስ በአዲስ አበባ ስታዲም 10፡00 ላይ ይገናኛሉ፡፡

የሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ መቐለ በ35 ነጥብ ይመረዋል፤ ሲዳማ ቡና በ30 ይከተላል ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ26 ነጥቦች ሶስተኛ እንዲሁም ፋሲል በ25 ነጥቦች አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

ደቡብ ፖሊስ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *