ከንቲባ ታከለ ኡማ በመዲናችን አዲስ አበባ ከሚኖሩ የሶማሌ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያዩ።
የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ተግባር የከተማውን ነዋሪ ህይወት መቀየር መሆኑን የገለፁት ኢ/ር ታከለ ኡማ የሶማሌ ማህበረሰብም የዚሁ አካል መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
በአዲስ አበባ ውስጥ የሚኖሩ ከ30ሺ በላይ የሚሆኑ የሶማሌ ማህበረሰብ አባላትም እንደ ከተማ ነዋሪነታቸው የስራ ዕድል ተጠቃሚ ፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕድል እና የመንግስት አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ እንደሚሰራም ኢ/ር ታከለ ኡማ ቃል ገብተዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ተቀራርቦ በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የኦብነግ አመራሮች፣ የጎሳ መሪዎች እና በርካታ የማህበረሰቡ አባላት ተሳትፈዋል፡፡