አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013 በሩሲያ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ:: የሩሲያ የፀጥታ ሃይሎች ከ3 ሺህ በላይ ተቃዋሚ ሰልፈኞችን ማሰራቸው ተሰማ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት በቅርቡ ከህመም ያገገሙት የተቃዋሚ መሪው አሌክስ ናቫልኒ ከእስር ይፈቱልን የሚል ጥያቄ ይዘው ነው፡፡
አዲስ አበባ፣ጥር 17፣ 2013 የሊቢያ ተፋላሚ ኃይሎች ቁልፍ የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ እጩዎችን ለመምረጥ ተስማሙ ::የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች ሞሮኮ ላይ ባደረጉት አዲስ ውይይት የእጩዎቹ የምልመላ ሂደት ከማክሰኞ ጀምሮ እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡ ተፋላሚ ሃይሎቹ የደረሱበት ስምምነት በሀገሪቱ ለአስር ዓመታት የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት እንዲያበቃ ለማድረግ ሁነኛ መፍትሄ መሆኑ ነው የተመገረለት፡፡ ሂደቱ እስከመጭው ፌብሩዋሪ 2 ቀን ድረስ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከፍተት ያለባቸው ስትራቴጂያዊ ቦታዎንች በፍጥነት ለመሙላት ያለመ ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ከሚመረጠው አስፈፃሚው አካል ጋር በትብብር…
አዲስ አበባ፣ጥር 16፣ 2013 ግብፅ በመላ ሀገሪቱ ጣለችውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአስራአምስተኛ ጊዜ አራዘመች:: በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ተግባዋ የሚሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አቃጅ ዳግም የታደሰው በፓርላመው ውሳኔና በፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ይሁንታ ነው፡፡ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ግብፅ የመጀመሪያውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣለቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 ነበር፡፡ በወቅቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተደነገገው የሽበርተኝነትን አደጋ ለመከላከል በሚል ምክንያት ሲሆን አሁንም ድረስ ስጋቶች ባለቀረፋቸው ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ተራዝሟል ነው የተባለው:: ግብፅን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ ካበቋት ሁኔታዎች መካከል…