የኤርትራ እና የኢትዮጲያ በጋራ የመስራት ቁርጠኝነት አሰብን እስከመካፈል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
የኤርትራ እና የኢትዮጲያ በጋራ የመስራት ቁርጠኝነት አሰብን እስከመካፈል ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ
የአውሮፓ ህብረት በጋዛ ሰርጥ ያለው ውጥረት ያሳስበኛል አለ፡፡
የአውሮፓ ህብረት በጋዛ ሰርጥ ያለው ውጥረት ያሳስበኛል አለ፡፡ የህብረቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሀላፊ ፍሬዴሪካ ሞጎሮኒ እንዳሉት በአካባቢው የሚደረጉ የሮኬት ተኩስ ልውውጦችና እስራኤል የምትወስደው የአጸፋ እርምጃ አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልገዋል፡፡ አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከ2014 ጀምሮ እየተባባሰ የመጣው የአካባቢው ውጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል ሞጎሮኒ፡፡ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ካውንስል ባደረገው ስብሰባ ጉዳዩን በአጀንዳነት ቀድሞ ባይዘውም […]
የአሰብ ወደብ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር የኤርትራና የኢትዮጲያ መንግስታት መመሪያ ሰጡ፡፡
የአሰብ ወደብ በአፋጣኝ ስራ እንዲጀምር የኤርትራና የኢትዮጲያ መንግስታት መመሪያ ሰጡ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳሉት ከትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ማሪታይም አገልግሎት ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትናሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት እንዲሁም ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አካላት ያሉበት ግብረ ሀይል የአሰብን ወደብ ስራ ቶሎ ለማስጀመር ተቋቁሟል። የአሰብ ወደብን ለመጠቀም በአሁኑ ወቅት የመንገድ ጥገና […]
የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዕርቀ ሰላም ልዑኳን ወደ አሜሪካ ሸኘች፡፡
የኢትጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የዕርቀ ሰላም ልዑኳን ወደ አሜሪካ ሸኘች፡፡ በውጭ አገር ከሚኖሩ ብፁዓን አባቶች ጋር እየተደረገ ባለው የዕርቀ ሰላም ሂደት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ለዕርቀ ሰላም ልዑካን አባላት የሽኝት መርሐ-ግብር ተደርጎላቸዋል፡፡ አቡነ ማትያስ በሽኝት ስነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ዕርቀ ሰላም ሂደት የበኩሏን ጥረት ስታደርግ መቆየቷን […]
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በአሜሪካ በሚያደርጉት ቆይታ ከ40 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተባለ፡፡ በዋሽንግተንዲሲ፣ በሎሳንጀለስና በሚኔሶታ በሚካሄዱ የድጋፍ ሰልፎችም የተለያዩ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲ በሚደረገዉ የድጋፍ ሰልፍ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ የሚሳተፍበት ሲሆን ፤በሎሳንጀለስ ደግሞ የጥያቄና መለስ የዉይይት መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡ በሚኔሶታ በሚደረገዉ ሶስተኛዉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቆይታ የተለያዩ ፖለቲካዊ […]
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነገ ወደ አሜሪካ ይሄዳሉ
“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩንም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚያደርጉት ጉዞ በአጠቃላይ በአሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን፥ በሀገራቸው እየተካሄደ ላለው ሁለንተናዊ ለውጥ አካል ሆነው ለሀገሪቱ ልማትና እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ያለመ ነው ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሎስ አንጀለስ እና በዋሽንግተን ዲ ሲ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ይወያያሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ሐምሌ 24 ቀን ድረስ ነው በአሜሪካ ቆይታ የሚያደርጉት። የኢፌዴሪ […]
ሺ ጂፒንግ ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል
የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ለብሪክስ ስብሰባ ነው ደቡብ አፍሪካ የተገኙት፡፡ ፕሬዝዳንቱ በመካከለኛው ምስራቅና በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ጉብኝታቸውን የጀመሩ ሲሆን ከነገ ጀምሮ እስከ ዓርብ ድረስ በሚካሄደው 10ኛው የብሪክስ ጉባዔ ይሳተፋሉ፡፡ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይናና ደቡብ አፍሪካ በጋራ ያቋቋሙት የትብብር ተቋም በዋናነት በሀገራቱ መካከል ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት ታስቦ ነው የተመሰረተው፡፡ ፕሬዝዳንት ሺ ጆሀንስበርግ በምታስተናግደው በዚህ ጉባዔ […]
መሪዎቹ ሜዳልያ ተሸለሙ
በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ነኸያን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ለኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሰላም እንዲሰፍን ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሀገሪቱን ፕሬዚዳንታዊ ሜዳሊያ ሸለሙ።