loading
አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ

አቶ በረከት ስምኦን እና አቶ ታደሰ ካሳ ዛሬ በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡ በጥረት ኮርፖሬት ፈጽመዋል ተብሎ በተጠረጠሩበት የሀብት ብክነት ወንጀል አዲስ አበባ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ የዜናው ምንጭ አማራ መገናኛ ብዙሃን ነው። ዝርዝር ዜናው እንደደረሰን እናቀርባለን።

የህጻናትን ጤንነት ላይ መንከባከብ ሀገርን የማስቀጠል ዋስትና መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ

የህጻናትን ጤንነት ላይ መንከባከብ ሀገርን የማስቀጠል ዋስትና መሆኑን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ። ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት በኪዩር ኢትዮጵያ ሆስፒታል የ10ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ በተገኙበት ወቅት ነው። ኪዩር ኢትዮጵያ ከረጂ ድርጅቶችና ከኢትዮጵያውያን በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር ባለፉት 10 ዓመታት ከጡንቻና ከአጥንት ችግር ጋር በተያየዘ አካል ጉዳተኛ ሆነው ለተወለዱ ህፃናት 17 ሺህ የህፃናት ቀዶ ህክምና ማድረጉን ያሳወቀ […]

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት እንደሚደግፍ ገለጸ

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ያለውን ልማት እንደሚደግፍ ገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በዳቮስ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዜዳንት ፒተር ማዉረር ጋር ተወያይተዋል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፎች በታየው ለውጥ ምክንያት ተስፋ መታየቱን ተናግረው ዓለም አቀፉ የቀይ […]

ለስድስት ወራት በቆየው የምህረት አዋጅ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ

ለስድስት ወራት በቆየው የምህረት አዋጅ ከ13 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለፀ። ሀምሌ 13 2010 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ የገባው የምህረት አዋጅ ከትናንት በስቲያ ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም ተጠናቅቋል። የምህረት አዋጁ ተፈፃሚ ሆኖ በቆየባቸው የስድስት ወራት ጊዜያትም ከ13 ሺህ 200 በላይ ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታውቋል። አዋጁ […]

በድሬዳዋ የተፈጠረው ግጭት ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም ተባለ

በድሬዳዋ የተፈጠረው ግጭት ከሃይማኖት ጋር ግንኙነት የለውም ተባለ ጥር 12 እና 13 በድሬዳዋ ከተማ የተከሰተው የወጣቶች ጸብ ከኃይማኖት ጉዳይ ጋር ግንኙነት እንዳልነበረው የከተማዋ የኃይማኖት አባቶች ተናገሩ። የክርስትናና የእስልምና ኃይማኖት አባቶች ግጭቱን አስመልክቶ ትናንት በሰጡት መግለጫ የሃይማኖት አባቶቹ እንደተናገሩት ግጭቱን የፈጠሩ አካላትም ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ። የድሬዳዋ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ […]

የመንግስት አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ኤሌክትሮኒክስ አውታር ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው

የመንግስት አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ኤሌክትሮኒክስ አውታር ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። ስርዓቱ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው መረጃ ለመለዋወጥ፣ የንግድ ስምምነት ለመፈፀም፣ የንግድ ስራዎችን ለመምራት፣ ለመማርና ሌሎች መንግስታዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡ የመንግስት ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎቱ የፌደራል፣ ክልል፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ወረዳና ቀበሌን በማስተሳሰር ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀልጣፋና የማይቆራረጥ አገልግሎት ለመስጠትም የሚያስችል ነው ተብሏል። አገልግሎቱን ለመጀመር የመሰረተ ልማት ለመግንባት […]