የኢሚሊያኖ ሳላ ህልፈተ ህይወት ከተሰማ በኋላ የስፖርት ቤተሰቡ ሀዘኑን እየገለፀ ነው
የሳላ ህልፈት ቢሰማም የአብራሪው ኢቦትሰን አካል ባለመገኘቱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡
የሳላ ህልፈት ቢሰማም የአብራሪው ኢቦትሰን አካል ባለመገኘቱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡
ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የሱዳንና እንግሊዝ ዜጋ የቢዝነስ መሪና የሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን መስራች የሆኑትን ዶ/ር መሃመድ ኢብራሂም ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ሁለቱ ወገኖች ስለአስተዳደር፣ ስለ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትና በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ ስላሉ ተያያዥ ችግሮች ተወያይተዋል። እንዲሁም ወሳኝ የሆነው አህጉራዊ የወጣቶች ተሳትፎና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ተወያይተዋል። ዶ/ር መሃመድ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በማድነቅ አንድነት ላይ ተመስርቶ ተጠናክሮ […]
የመማር ማስተማሩ ሂደት ተቋርጦ የነበረው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከፊታችን ሰኞ የካቲት 4 ጀምሮ ተማሪዎች ተመልሰው ትምህርት እንዲጀምሩ በሴኔት መወሰኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ለሚ ጉታ እንደተናገሩት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና መምህራን ትናንት ከተማሪ ወላጆች ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ሴኔቱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ወስኗል ብለዋል። ከተማሪ ወላጆች ጋር በተደረገ ውይይትም ወላጆች ተማሪዎች ጥያቄ […]
አሁን በደረሰን ዜና በድሬዳዋ ከነበረው ሁከትና ግጭት በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ 54 ተጠርጣሪዎች ከህብረተሰቡ ጋር ከሚካሄድ ውይይት ጋር ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ሊለቀቁ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል። ኮሚሽኑ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው ከሚለቀቁት ተጠርጣሪዎች ጋር ውይይት ይካሄዳል። በትናንትናው ዕለት 32 ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ምርመራቸው ተቋርጦ ከእስር የተፈቱ መሆኑ ይታወሳል። በቀጣይ ቀናትም እየተጣሩ ያሉ የምርመራ […]
በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ የሆነው African Renaissance and Diaspora Network የተባለ ተቋም ኢ/ር ታከለ ኡማን የአፍሪካ የከንቲባዎች እና መሪዎች አለም አቀፍ ትብብር ፤ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ አድርጎ መረጠ፡፡ የተቋሙ ፕረዝዳንት ዶ/ር ጂብሪል ዲያሎ ኢ/ር ታከለ ኡማ በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየሰሩት ባለው የልማትና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ስራዎች እና የጎዳና ላይ […]
የገቢዎች ሚኒስቴር በደቡብ ክልል የገቢ ግብር ንቅናቄ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ። በቅርቡ የተካሄደው የትግራይና አማራ ክልል የገቢ ግብር ንቅናቄ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁንና ውጤታማ ስራ መሰራቱንም ተናግሯል። በሀገሪቱ ግብር መክፈል ከነበረባቸው ዜጎች መካከል የሚከፍሉት 60 በመቶ ያህሉ ብቻ መሆናቸውን የተናገሩት የገቢዎች ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ይህንን ለማሻሻል ሚኒስቴሩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። ግብር ለሃገሬ በሚል መሪ […]
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በተፈጠረ ግጭት እስካሁን 39 ሺህ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በሰውና ንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በአማራና ቅማንት ብሄረሰቦች መካከል በተቀሰቀሰና እስካሁን መብረድ ባልቻለ የስርበርስ ግጭት እስካሁን 39 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መሰደዳቸውና በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ታውቋል። የክልሉ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ […]
የጋምቤላ ክልል ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ሹመቶችንና አዋጆችን አጸደቀ፣የአስፈጻሚ መስሪያ ቤቶችን ቁጥርም ከ21 ወደ 18 ዝቅ አድርጓል። ለሶስት ቀናት የተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የክልሉን የፋይናንስ አስተዳደር ዓዋጅና የተሻሻለውን የአስፈጻሚ አካላትን አደረጃጀት ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ ዓዋጅ አጽድቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፣ የዋና ኦዲትና የአስፈጻሚ መስሪያ ቤት ኃላፊዎችን፥ እንዲሁም ከክልል እስከ […]
ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ስልጠናውን የሰጠው ከፌደራል፣ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ 70 የስራ ስምሪት ባለሙያዎች ነው። በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ብርሀኑ አበራ እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ ለሥራ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው መስራት የሚፈልጉ ዜጐች ህግና ሥርዓትን ተከትለው በመሄድ በሚሰሩበት አገር መብታቸው፣ ደህንነታቸውና […]
ናይጀሪያ የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ምርጫየን ሊታዘቡ ይችላሉ ብላለች፡፡ የፕሬዝዳንት ሙሀማዱ ቡሀሪ ረዳት ናስር አል ሩፋይ በሀገራችን የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት የሚሞክር ማንኛውም አካል ወደ መጣበት ይመለሳል የሚል ማጠንቀቂያ በሰጡ ማግስት ነው አቡጃ ይህን ያለችው፡፡ አል ሩፋይ መግለጫውን በሰጡበት ወቅት እኛ ለሀገራችን ምን መስራት እንዳለብን ሊያስተምረን የሚመጣ ሰው የለም ነው ያሉት፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ […]