የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የተቀናጀና ትብብርን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ” ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ
በኢትዮጵያ የሴቶችን ተጠቃሚነት እና እኩልነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ተግባራትን ውጤታማ ለማድረግ የተቀናጀና ትብብርን መሰረት ያደረገ እንቅስቃሴ እንደሚያስፈልግ ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አስገነዘቡ። “መተባበር ለላቀ ውጤት” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው እና በሥርዐተ ጾታ እኩልነት እና ሴቶችን በማብቃት ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የውይይት መድረክ በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ ዛሬ ረፋድ ላይ ሲጀመር ፕሬዚዳንቷ እንዳሉት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተፈጠረውን መልካም […]