የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትርና የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ተወያዩ
የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ማውረን አቺንግ ጋር በሁለትዮሽ የትብብር ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ ምክክራቸውም ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው መለወጥ በሚችሉበት ሁኔታ፣ እንዴት በህጋዊ መንገድ ለሥራ መጓዝ እንደሚችሉ ግንዛቤ በመፍጠርና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም ሕጋዊ የውጭ አገር የሥራ ስምሪትን የማጠናከር […]