loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ   ጠቅላይ ሚኒስትር ሚር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ተመለሱ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጣሊያን የጀመሩትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ስዊዘርላንድና ቤልጂየምን በማካለል ተጠናቅቋል፡፡ በጉብኝቱም ከተለያዩ አገራት መሪዎችና የቢዝነስ አንቀሳቃሾች ጋር በመምከር የሁትዮሽ ግንኙነትን ከማጠናከር ባለፈ ኢትዮጵያን በኢንቨስትመንትና ማገዝ የሚያስችሉ ስምምነቶች ተፈርመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአውሮፓ ህብረት […]

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ኦነግ ተኩስ ለማቆም ተስማሙ። የኦነግ ሠራዊት ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትና ኦነግ ተኩስ ለማቆም ተስማሙ። የኦነግ ሠራዊት ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል። ሁለቱም አካላት ስምምነቱን የፈጸሙት አምቦ ላይ በተካሄደው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና የኦነግና የእርቀ ሠላም ጉባዔ ላይ ነው። በስምምነቱ የኦነግ ሠራዊት በ20 ቀናት ውስጥ ትጥቅ ፈትቶ ወደ ካምፕ እንዲገባ ውሳኔ ተላልፏል። በሁለቱ ፓርቲዎች መካከል እርቅ ለማውረድ በአዲስ አበባ በተካሄደው ጉባኤ […]

የሀገር ሽማግሌዎቹ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ተስማሙ

የሀገር ሽማግሌዎቹ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት ተስማሙ። ሰሞኑን በአፋርና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና የሀገር ሽማግሌዎች መስማማታቸው ተገለጸ። በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣  የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱም የተፈጠረውን ግጭት  ለመፍታት የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት መሪዎችና […]

በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ አምባሳደሮች በሃገሪቱ የሚካሄደውን የለውጥ ሂደት እንደሚደግፉ አስታወቁ

በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ አምባሳደሮች በሃገሪቱ የሚካሄደውን የለውጥ ሂደት አእንደሚደግፉ አስታወቁ።   በኢትዮጵያ የተጀመረውን የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ለውጥ እንደሚደግፉ በአገሪቱ አዲስ የተሾሙ የስምንት አገራት አምባሳደሮች  ገለፁ። አምባሳደሮቹ ይህንን የተናገሩት በብሄራዊ ቤተ መንግስት  ቀርበው ለፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ነው። አዲስ ተሿሚዎቹ  የካናዳ፣የቱርክ፣ የሴራሊዮን፣ የኢኳቶሪያል ጊኒ፣ የስሎቫኪያ ሪፐብሊክ፣ የሰርቢያ እንዲሁም ተቀማጭነታቸው በካይሮ እና ናይሮቢ ያደረጉት […]

በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ ወረቀት አልባ የህክምና ና የጤና መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ ሊሆን ነው ተባለ

በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ ወረቀት አልባ የህክምና ና የጤና መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ ሊሆን ነው ተባለ በኢትዮጵያ  በኤሌክትሮኒክስ የተደገፈ ወረቀት አልባ የህክምና ና የጤና መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የዲጂታይላይዜሽን የጤና አገልግሎት ሥርዓትን ያስተዋወቀበትን መርሐ ግብር በመቀሌ ከተማ ባካሄደበት ወቅት እንዳስታወቀው ሥርዓቱ በሙከራ ደረጃ በትግራይ፣ በአማራ፣በኦሮሚያና በደቡብ ክልሎች በሚገኙ 1ሺህ60 የጤና ተቋማት ላይ ተጀምሯል፡፡ […]

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ለደንበኞቼ ቀልጣፋ አገልግሎት ተዘጋጅቻለሁ አለ

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ለደንበኞቹ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ ድርጅቱ 13 ዘመናዊ የኮንቴይነር መጫኛና ማውረጃ ማሽኖችን ለስራ ማዘጋጀቱ ተነግሯል። የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት 95 በመቶው የሀገሪቱ ገቢና ወጪ ንግዶች ይከናወኑበታል፡፡ በሰባት ደረቅ ወደብና ተርሚናሎች ነው እያገለገለ የሚገኘው፡፡ ድርጅቱ በ11 የኢትዮጵያ መርከቦች ከ306 ያላነሱ የተለያዩ ሀገራት ወደቦችን በማዳረስ ዕቃዎችን ያጓጉዛል፡፡ የድርጅቱ የኮርፖሬት […]

17ኛው የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው

17ኛው የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በጂንካ ከተማ እየተከበረ ነው።  በክብረ በዓሉ ላይ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፤ የሰላም ሚንስትሯ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል። በዚህ በ17ኛዉ የኢትዮጵያ አርብቶ አደሮች ቀን በሚከበርበት ወቅት በጂንካ የተገኙት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአርብቶ አደሩ አካባቢ የመልማት ግብን ለማሳካት መንግስት ውኃን መሰረት አድርጎ እንደሚሰራ  ተናገረዋል፡፡ […]