loading
የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ላይ ይበልጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናገሩ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2012 የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ላይ ይበልጥ መስራት እንደሚያስፈልግ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ተናገሩ፡፡ ይህንን ያሉት ከምክርቤቱ 14ተኛ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን የጤና ሚኒስትርና  የህብረተሰቡ ጤና  እንስቲትዮት በሀገሪቱ ቫይረሱን በተመለከተ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች በአብራሩበት ወቅት ነዉ ፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየብስ በአየርም 520 ሺ የሚሆኑ መንገደኞች ወደ ሀገር የገቡ ሲሆን 958ቱ […]

ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገር ሠላምና ዘላቂ ልማት መቆም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡

ልዩነትን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ለሀገር ሠላምና ዘላቂ ልማት መቆም እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጹ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  አቶ ደመቀ መኮነን በባህር ዳር “የጋራ ራዕይና ግብ ለአማራ ሕዝብ ዘለቄታዊ አንድነትና ሁለንተናዊ ስኬት” በሚል መሪ ሐሳብ  በተካሄደዉ ጉባኤ ላይ አንደተናገሩት የታፈረች ሀገር መመሥረት የሚቻለው በትንንሽ አጀንዳዎች ላይ ጊዜን በማጥፋት ሳይሆን ትላልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት […]

ኮሮናቫይረስ ያለበት ጃፓናዊ በኢትዮጵያ መገኘቱ የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታወቀ።

ሚኒስትሯ ዛሬ ከሰዓት በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት አንድ ከሶስት ቀን በፊት ከቡርኪናፋሶ ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል። ከዚህ ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ታከለ ኡማ በትዊተር ገፃቸው ላይ አንድ ጃፓናዊ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶበታል ሲሉ አስታውቀው ነበር። ከንቲባው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መውሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄ በመልዕክታቸው ላይ ጨምረው አስፍረዋል። ሚኒስትሯ እንዳሉት ጃፓናዊ ትኩሳትና ማሳል የመሳሰሉ […]