loading
“ፈጠራ በቀውስ ጊዜ” የአዲስ ወግ ዌቢነር ውይይት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሄደ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 “ፈጠራ በቀውስ ጊዜ” የአዲስ ወግ ዌቢነር ውይይት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሄደ:: በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በተካሄደዉ ዉይይት  በቀውስ ጊዜ የሚፈጠሩ አዳዲስ ችግሮችን ማለፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አተኩሯል፡፡ችግር ለፈጠራ መንስኤ በመሆኑ ችግር ፈቺ ፈጠራዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ የቪዲዮ ኮንፈረንሱ አወያይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ተናግረዋል።ሁሉም ስብሰባዎች በቪዲዮ ኮንፈርንስ እንዲደረጉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ውይይቶች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት እየተካሄዱና በቀጣይ የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር የሚያግዙ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲጸድቅ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።የኢ-ኮሜርስ፣ ኢ-ሰርቪስ፣ የኢ፤ትራንዛክሽን አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች መላኩንም ተናግረዋል።እነዚህን አገልግሎቶች በፍጥነት ስራ ላይ ለማዋል እየተሰራ ሲሆን ከ30 በላይ በቴክኖሎጂ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ያላቸውን የቴክኖሎጂናአማራጭ እንዲያቀርቡ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።የመንግስት ተቋማትን እናአገልግሎት ፤ሰዎች በያሉበት ሆነው ለማግኘት እንዲችሉ “የኢ-ሰርቪስ” አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የፈጠራ ስራ እየሰሩ ያሉ ሰዎች ለሚኒስቴሩ እንዲያቀርቡ እና እውቅና እንዲያገኙ ሁኔታዎች መመቻቸቱንም ጠቁመዋል።

 ባለስልጣኑ  ሰባት መንገዶችን በአስፓልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት አካሔደ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 ባለስልጣኑ  ሰባት መንገዶችን በአስፓልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት አካሔደ። የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ከ11 ነጥብ ስድስት ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ ሰባት መንገዶችን በአስፓልት ደረጃ ለመገንባት የሚያስችል የውል ስምምነት ማከሄዱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡የውል ስምምነት የተፈረመላቸው ሰባት መንገዶች በጥቅሉ ከ500 ኪ.ሜ በላይ ርዝመት አላቸው።ለግንባታቸው የሚውለው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት የሚሸፈን መሆኑ […]

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለአራት ቀናት በተካሄደ የእርስ በርስ ግጭት 43 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለአራት ቀናት በተካሄደ የእርስ በርስ ግጭት 43 ሰዎች መሞታቸው ተነገረ፡፡አጃንስ ፍራንስ ፕረስ የወታደር ባለስልጣናትን ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክፍል በሚገኙ ሁለት ግዛቶች በተፈጠረ ግጭት 43 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡በግጭቱ አርብ እለት ጥቃት አድራሾች ስለትና የጦር መሳሪያ በመጠቀም 21 ንጹሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነው አጃንስ ፍራንስ ፕረስ የዘገበው፡፡ በድንበር አቅራቢያ […]