loading
ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና “ የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና “ የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ::በኮቪድ19 ምክንያት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ አስቸጋሪ በመሆኑ መንግስት አራት የመፍትሄ አማራጮችን አቅርቧል።“ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት መንግስት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር  ነዉ ውይይት ያካሄደዉ፡፡ ኢትዮጵያ በህገ መንግስቱ መሰረት እስከ ነሃሴ […]

የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ:: የቱርክ መንግስት ለኮቪድ -19 ወረርሽኝ መከላከል ተግባር የሚውሉ  ድጋፍ ያደረጉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡ድጋፉ በዋነኝነት ለኮቪድ 19 በሽታ መከላከያ ተግባር የሚውሉ ሲሆን 280 ካርቶን ወይም 1 ሺህ 700 ኪሎ ግራም የሆነ የንጽሕና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣ […]

ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 ሞሮኮ በማረሚያ ቤቶቿ ባደረገችው ምርመራ ከ300 በላይ ታራሚዎች በኮቪድ 19 መያዛቸውን አረጋገጠች:: ይሄ ቁጥር የተገኘው በሶስት እስር ቤቶች በሚገኙ 1 ሺህ 736 እስረኞች ላይ በተደረገ ምርመራ መሆኑን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ከነዚህ ሶስት እስር ቤቶች መካከል ደግሞ 303 በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች የተገኙት በሀገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በሚገኝ ኦዋራዛቴ […]

በማሊ የሥደተኞች ጣቢያ በእሳት በመውደሙ ዜጎች ለሁለተኛ ስደት ተጋልጠዋል::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2012 በማሊ የሥደተኞች ጣቢያ በእሳት በመውደሙ ዜጎች ለሁለተኛ ስደት ተጋልጠዋል:: በማሊ በተከሰተው የርስበበርስ ግጭት ምክንያት መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው በጊዜያዊ መጠለያ የነበሩ ሰዎች መኖሪያቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተሰምቷል፡፡አሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው በዚህ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ እስከ ሁለት ዓመት የቆዩ ከ1 ሺህ በላይ የሚሆኑ ማሊያዊያን ስደተኞች ይኖሩ ነበር፡፡ ስደተኞቹ እንደተናገሩት አለን […]