loading
በዉጪ የሚገኙ ትውልደ  ኢትዮጵያዉያን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚዉል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ፡፡

በዉጪ የሚገኙ ትውልደ  ኢትዮጵያዉያን ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚዉል ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ ፡፡ አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 በተለያዮ የዓለም ሀገራት የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁም ከሚሲዮኖች ሰራተኞች ከ100 ሚሊዮን ብር  በላይ መሰብሰቡን የብሄራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታዉቋል፡፡ድጋፉ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በውጭ በሚገኙ 60 ሚሲዮኖች መሰባሰቡ ተጠቁሟል፡፡ ድጋፉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ እንዳርጋቸው ተረክበዋል።ሚኒስትሩ በዚህ  ወቅት ድጋፉ አገር በችግር ውስጥ ባለችበት ጊዜ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያደረጉት በመሆኑ አመስግነዋል። በተለይ ራሳቸው ችግር ውስጥ ሆነው አገራቸውን እየረዱ ያሉ ወገኖች እንዲሁም ሚሲዮኖች እያደረጉ  ላለው  ድጋፍ  አድናቆታቸውን ገልጸዋል።በሀገር ዉስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ይሁን በዉጪ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያዉያን  ቫይረሱን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት […]

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2012 የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥን ጎበኙ:: የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመናኸሪያ አገልግሎት አሰጣጥንና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ በማለዳ ጎብኝተዋል። የአስኮ፣ የመርካቶና የአየር ጤና መናኸሪያዎች የአገልግሎት አሰጣጥን ነዉተዘዋውረው የተመለከቱት በጉብኝታቸውም ተገልጋዮችን ሹፌሮችና ሌሎችንም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ስርጭት ለመከላከል ስለሚያደርጉት ጥንቃቄና ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ የአነጋግረዋል።በተለይ በአገሪቱ የኮቪድ 19 ቨይረስን ለመከላከል በትራንስፖርት ውስጥ እየተደረገ ያለውን ጥንቃቄና የኬሚካል ርጭት ተመልክተዋል።የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ ድንጋጌ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

ደቡብ አፍሪካ የቲቢ ክትባትን ኮቪድ 19ን ለመከላከል  ይውል ዘንድ ሙከራ መጀመሯን ይፋ አደረገች፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 ደቡብ አፍሪካ የቲቢ ክትባትን ኮቪድ 19ን ለመከላከል  ይውል ዘንድ ሙከራ መጀመሯን ይፋ አደረገች፡፡የጤና ባለሙያዎች ለኮቪድ 19 ክትባት ለማግኘት የምርመርና የሙከራ ስራ በመስራት መጠመዳቸው ነው የተነገረው፡፡አምስት መቶ የጤና ባለሙያዎች ለዚሁ ስራ የተመደቡ ሲሆን የክሊኒካል የምርመር ተቋማት ደግሞ የምርምር ስራዉን በገንዘብ ይደግፋሉ ተብሏል፡፡በኬፕታውን  ክትባቱ የሚሞከርባቸው 3ሺ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ተዘጋጅተው ለአንድ ዓመት […]

ናይጄሪያ የእንቅስቃሴ እገዳ ባነሳች በሰዓታት ውስጥ የታማሚዎች ቁጥር በ245 መጨመሩ ድንጋጤን ፈጥሮባታል::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2012 ናይጄሪያ የእንቅስቃሴ እገዳ ባነሳች በሰዓታት ውስጥ የታማሚዎች ቁጥር በ245 መጨመሩ ድንጋጤን ፈጥሮባታል::የሀገሪቱ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል እንዳለው በናይጄሪያ ከአሁን በፊት በአንድ ቀን ውስጥ ይሄን ያህል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበው አያዉቁም፡፡ናይጄሪያ ለስድት ሳምንታት ያህል ጥላው የቆየችውን የእንቅስቃሴ እገዳ ያላላችው የበሽታው ስርጭት የመቀነስ አዝማሚያ በማየቱ ነበር፡፡ይሁን እንጂ ተዘግተው የነበሩ የንግድ እና ሌች አገልግሎት […]