loading
የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012 የብሩንዲ የምርጫ ኮሚሽን ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የድምፅ ቆጠራ ውጤቱን በትግዕስት እንዲጠብቁጥሪ አቀረበ ብሩንዲያዊያን ባለፈው ረቡዕ የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ሳያስፈራቸው የወደፊት ፕሬዚዳንታቸውን ወደ ስልጣን ለማምጣት የሚያስችላቸውን ድምፅ ሲሰጡ ታይተዋል፡፡ የብሩንዲ ብሄራዊ ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቆጠራው ገና ቀናትን ስለምወስድ ከወዲሁ የሚተላለፉ የአሸናፊነት መልእክቶች እንዲቆሙ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡ ይሁን እና የተቃዋሚ መሪው አጋቶን ሩዋሳ የድምጽ ቆጠራው […]

1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል አርብ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ካልሆነ ግን እሁድ ይከበራል፡፡

1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል አርብ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ  ካልሆነ ግን እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታዉቋል፡፡የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ለምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በዕለቱ የጀምዓ ሶላት እንደማይኖር የገለጹት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ምእመናን በዓሉን በየቤታቸው እንዲያከብሩት አሳስበዋል፡፡  ምእመናን በዓሉን የተራቡትን በማጉረስ፣ የተጠሙትን በማጠጣት በአጠቃላይ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር የቴንሴንት ፋውንዴሽን የላካቸውን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶች ተረከበ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012  ጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ እነዳስታወቁት  የቴንሴንት በጎ አድራጎት ድርጅት ኮቪድ19 ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚሰራውን ስራ ለማገዝ የሚያስችሉ 1ነጥብ6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የመመርመሪያ ኪቶችንና ጓንቶችን ድጋፍአድርጓል፡፡ ዶ/ር ሊያ በጎ አድራጎት ድርጅቱ  ስላደረገልን ድጋፍ ልባዊ ምስጋናዬን እየገለጽኩ ሁሌም ትብብራቸው የማይለየንን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድን ላመሰግንን እወዳለሁ ብለዋል  በፌስቡክ ገጻቸዉ፡፡ የቴንሴንት ኩባንያ የታዋቂው […]

የኮሮና በሽታን ለመከላከል የሚያስችሉ ፈጠራዎችን ያቀረቡ ተወዳዳሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተበረከተላቸዉ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣2012  የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ጋር ባደረጉት የድጋፍ ስምምነት እና በመንግስት እገዛ ሲካሄድ የነበረው የኮቪድ 19 ቴክኖሎጂ ሶሊዩሽን ቻሌንጅ ዉድድር ተለይተዉ ታዉቀዋል።  በአጭር  ጊዜ ተተግባሪና መፍትሔ ሊያመጡ የሚችሉት ምርጥ ፕሮጀክቶች ተለይተው እውቅና ተሰጥቷቸዋል። ፍጻሜውን ያገኘውን የውድድር ሂደት በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽን ምርምር ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ በችግር […]