loading
የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 የቀድሞዋ የአሜሪካ ቀደማዊት እመቤት ሚሼል ኦባማ ትራምፕ አሜሪካን ከችግር የመታደግ አቅም የላቸውም አሉ:: ቀዳማዊት እመቤቷ ፕሬዚዳንቱ ውጤት ያለው ስራ ሰርቶ ለማሳየት ከበቂ በላይ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል ግን አንድም ፍርያማ ተግባር አላከናወኑም ብለዋል፡፡ ትራምፕ ለሀገራችን ትክክለኛው መሪ አይደሉም ያሉት ሚሼል አንድ ቀላል ምሳሌ ብናነሳ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በአሜሪካ የተከሰተውን ሁኔታ ማረጋጋት አልቻሉም […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስር ሹመቶችን ዛሬ ሰጡ:- – ዶ/ር ቀንዓ ያደታ የመከላከያ ሚኒስትር – ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ – ዶ/ር ሳሙኤል ሁርካቶ፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር – ታከለ ኡማ፤ የማዐድንና ነዳጅ ሚኒስትር – ተስፋዬ ዳባ፤ ምክትል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ – ዮሐንስ ቧያለው፤ የኢትዮጵያ የውጭ ግነኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት […]

በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ አገኙ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 በሊባኖስ የሚኖሩ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው ለመመለስ ፈቃድ አገኙ:: በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ቆንላ ጀነራል ተመስገን ዑመር ጽሕፈት ቤቱ በሊባኖስ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች መረጃዎች ለአገሪቱ ኢምግሬሽን ጉዳዮች መሥሪያ ቤት አስገብቶ እንደነበር ለኢዜአ ገልጸዋል። በዚሁ መሠረት የኢሚግሬሽን ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ 450 ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ፈቃድ […]

ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ኢንጂኔር ታከለ ኡማ በከንቲባነት ዘመናቸው ላደረጉላቸው ድጋፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን አመሰገኑ:: ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ቦታቸው ተቀይረው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሆነው የተሸሙትምክትል ከንቲባው በነበራቸው የሁለት ዓመት የሥራ ዘመን የከተማዋ ነዋሪዎች እና የስራ ባለደረቦቻቸው ድጋፍ እንዳልተለያቸው በፅህፈት ቤታቸው ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ አስፍረዋል፡፡ በታሪክ አጋጣሚ ይህችን ታሪካዊ ከተማ ለመምራት የተገኘውን ትልቅ ዕድል ላለማባከን […]

ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 12፣ 2012 ሱዳናዊያን በሀገሪቱ የስልጣን መጋራት ስምምት የተደረገበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ሰልፍ አካሂደዋል:: ነዋሪዎቹ ካርቱም ውስጥ ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ አሁን ባለው የሉዓላዊ ምክር ቤት አስተዳደር ቅሬታ እንደገባቸው ተናግረዋል፡፡ ሰልፈኞቹ አደባባይ የወጡት ፕሬዚዳንት አልበሽርን በሃይል ከስልጣናቸው ያስወገዱት ጄኔራሎችና ህዝቡን ወክለው ስልጣን የተጋሩት ፖለቲከኞች ሀገር መምራት ከጀመሩ አንድ ዓመት ቢያስቆጥሩም የተፈለገው ለውጥ አልመጣም በማለት ነው፡፡ […]