loading
የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 የሞሳድ ሹም በአቡዳቢ የእስራኤሉ ሞሳድ የስለላ ድርጅት ሀላፊ በደህንነት ዙሪያ ለመወያየት አቡዳቢ ገብተዋል:: ሀላፊው ዮሲ ኮኸን እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የዲፕሎማሲ ስምምነት ከተፈራረሙ ወዲህ አቡዳቢን የጎበኙ የመጀመሪያው ባለ ስልጣን ሆነዋል፡፡ ኮኸን ከኤሜሬቶች የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታኑም ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ሁለቱ ሀገራትበደህንነት እና ፀጥታ ዙሪያ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች […]

አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 አንድ የቻይና ከፍተኛ ዲፒሎማት በሁለቱ ኮሪያዎች ጉዳይ ለመምከር ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዙ ነው:: በሰሜን እና ደቡብ ኮሪያዎች መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው ውጥረት ተሟሙቆ የነበረውን አዲስ ግንኙነት ጥላ አጥልቶበታል፡፡ ሁለቱ ሀገራት በድንበር አካባቢ ቀለል ያለ የተኩስ ልውውጥ እስከማድረግ ያደረሳቸው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ሳያንስ ለሽምግልና በሮቻቸውን መዝጋታቸውም ስጋቱን ከፍ አድርጎታል፡፡ ከሴኡል […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በገበታ ለሀገር እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ የዛሬ ዓመት ቃል የገባነውን ፈጽመን በተግባር አሳይተናል ብለዋል። በገበታ ለሀገር ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የገንዘብ መጠን እንዲያዋጡ የተዘጋጀውን የባንክ ሂሳብም ይፋ አድርገዋል፡፡ በዚህም የ10 ሚሊየን እና የ5 ሚሊየን ብር ገቢ ለማድረግ እንዲሁም ከሀገር ውስጥ ማንኛውም […]

ስምንተኛዉ የበጎ ሰዉ ሽልማት መርሃግብር ጳጉሜ 1 ሊካሄድ ነዉ፡፡

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 13፣ 2012 ስምንተኛዉ የበጎ ሰዉ ሽልማት መርሃግብር ጳጉሜ 1 ሊካሄድ ነዉ፡፡ “በጎ ሰዎችን በማክበር እና እዉቅና በመስጠት ሌሎች በጎ ሰዎችን እናፈራለን” በሚል መረሃግብር በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን በአስር ዘርፎችም ለአገራቸዉ በሞያቸዉ የላቀ ተግባር ላበረከቱ ሰዎች ይበረከታል፡፡ የበጎ ሰዉ ሽልማት ድርጅት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ የዘንድሮ የሽልማት መርሀግብር ከየካቲት 1 አስከ መጋቢት 15 ከ200 በላይ […]