loading
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ሂደት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ ገለፀ:: ጠቅላይ አቃቤ ህግ በ2013 በጀት ዓመት ለማከናወን ባቀዳቸው ተግባራትና በአስር አመት መሪ እቅዱ ላይ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር መክሯል። በመድረኩም የህግ አወጣጥና አተገባበር፣ የሰብአዊ መብትና ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት ተደርጓል። በጠቅላይ አቃቤ ህግ […]

የምስራቅ ሐረርጌ አገረ ስብከት የመስቀል በዓል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚያከብር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 የምስራቅ ሐረርጌ አገረ ስብከት የመስቀል በዓል የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር እንደሚያከብር አስታወቀ:: በሐረሪ ክልል የደመራና የመስቀል በዓልን ሐይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ በአንድነትና እርስ በርስ በመደጋገፍ በጥንቃቄ እንደሚከበር ነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት የገለፀው። የምስቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጽህፈት ቤት የትምህርትና ስልጠና ክፍል ሃላፊ መልዓከ […]

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች። በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።ለሳምንታት በህመም ላይ የነበረችው አርቲስቷ ዛሬ ማለዳ ነው ማረፏ የተሰማው።የአርቲስቷ ስርዓተ ቀብር ነገ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈፀማል።