loading
ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 ዓለም ባንክ ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ::የባንኩ ዳሬክተሮች ቦርድ ይፋ ባደረገው መሰረት ለታዳጊ ሀገራት የኮቪድ 19 ክትባት ግዢና ለዜጎቻቸው ምርመራና እንክብካቤ የሚውል 12 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጽድቋል የገንዘብ ድጋፉ ለአንድ ቢሊዮን ሰዎች ክትባት ማዳረስ የሚያስችል ሲሆን የዓለም ባንክ እስከ ፈረንጆቹ […]

የመቀሌ ዩኒቨርስቲ በአትሌቲክስና በብስክሌት ስፖርቶች በዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፈው አንፀባራቂ ድል ላስመዘገቡ ሁለት ሴት ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት ትናንት አበረከተ ።

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 የመቀሌ ዩኒቨርስቲ በአትሌቲክስና በብስክሌት ስፖርቶች በዓለም አቀፍ ውድድር ተሳትፈው አንፀባራቂ ድል ላስመዘገቡ ሁለት ሴት ስፖርተኞች የማበረታቻ ሽልማት ትናንት አበረከተ ።ዩኒቨርሲቲው ለሴት ስፖርተኞቹ የእውቅና ምስክር ወረቀትና የአንገት ሀብል ሽልማት አበርክቶላቸዋል። ዩኒቨርሲቲው ሽልማት ካበረከተላቸው ሴት ስፖርተኞች መካከል በቅርቡ በስፔን ቫለንሽያ ከተማ በተካሔደው የአትሌቲክስ ውድድር በ5 ሺህ ሜትር ሩጫ የአለም ክብረ ወሰን የሰበረችው […]

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የከሰላውን አስተዳዳሪ ከስልጣናቸው አነሱ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2013 የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር የከሰላውን አስተዳዳሪ ከስልጣናቸው አነሱ:: ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሀምዶክ ባለፈው ሰኔ ወር የከሰላ ግዛት አስተዳዳሪ አድርገው ሾሟቸውን ሳልህ አማርን ከስልጣናቸው ያወረዷቸው በአካባቢው ከተነሳው የጎሳ ግጭት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው  ተብሏል፡፡ አማር ለግዛቲቱ የመጀመሪያው የሲቪል አስተዳዳሪ ሆነው ከተሸሙ ጀምሮ ቤጃ ከተባሉት ጎሳዎች ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ሲሆን ወደ ግዛቲቱ እንዳይገቡ […]