loading
የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን እንዳለባቸዉ ኮሚሽኑ አሳሰበ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን እንዳለባቸዉ ኮሚሽኑ አሳሰበ፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ፤ በቀጣይ በትግራ በሚደረጉ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ተግባራት በፌዴራል መንግሥቱ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የመጠበቅ ግዴታ የሚመራ እንዲሆን አሳስቧል፡፡ ኮሚሽኑ በተለይ መንግስት የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙና ተገቢው ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን የተቋረጡ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃና […]

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሰዉ በአንድ ቀን ከኮሮረና ቫይረስ ማገገሙ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ሰዉ በአንድ ቀን ከኮሮረና ቫይረስ ማገገሙ ተገለፀ፡፡ የጤና ሚኒስቴር በህዳር 21 ምሽት የ24 ሰዓቱን የኮሮና ቫይረስ ሁነታን በተመለከት በሰጠዉ መረጃ መሰረት በእለቱ በአንድ ቀን ዉስጥ አራት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ሶስት ሰዎች ከኮረና ቫይረስ አገግገመዋል፡፡ ይህም እንደ አገር ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 73 ሺህ 8 መቶ […]

ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልሎች ጋር የቀጣይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ፈጸመ።

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልሎች ጋር የቀጣይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ፈጸመ። የአካባቢ፣ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽኑ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከክልሎች ጋር የቀጣይ ዓመታት የአረንጓዴ አሻራና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃን ለማጠናከር የሚረዳ ስምምነት ማድረጉን አስታዉቋል፡፡ በሂደቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የክልሎችን ተሳትፎ በማሳደግ በአንድ በኩል የክልሎችን አቅም ለማጎልበት በሌላ […]

የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 የተሰናባቹ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ስኮት አትላስ የስራ መልቀቂያ አስገቡ፡፡ የፕሬዜዳንቱ የኮሮናቫይረስ ልዩ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ስኮት አትላስ በገዛ ፈቃዳቸውን ስራ መልቀቃቸውን የዋይት ሃውስ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡ የኮቪድ 19 በመከላከል ዙሪያ ከተቀሩት የግብረ ሃይል አባላት ጋር አራት ወራትን ከፈጀ ንትርክ በኋላ የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸው ነው የተነገረው፡፡የአትላስ […]

በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 በናይጄሪያ በደረሰ ጥቃት የሟቾች ቁጥር ከ100 በላይ ደርሷል ተባለ :: በአህመድ ላዋን የተመራው የናይጄሪያ ሴኔት ልዑክ፤ በሳምንቱ መጨረሻ በገበሬዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች በተገደሉበት፤ የሰሜን ምስራቅ ቦርኖ ጉብኝት አድርጓል ፡፡ በተፈፀመው ጥቃት 43 አርሶ አደሮች መገደላቸው የተዘገበ ሲሆን ከአከባቢው ባለሥልጣናት ተሻሽለው እየወጡ ያሉ አኃዛዊ መረጃዎች የሟቾች ቁጥር ወደ […]