የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ::
አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2013 የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት አዲስ የጥምር ፓርቲ ለመመሰረት መወሰናቸውን ይፋ አደረጉ:: ፕሬዚዳንት ፊሊክስ ሺሴኬዲ ይህን ያሉት በሳቸውና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ ፓርቲዎች መካከል አለመግበባት በመፈጠሩ ምክንያት ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው በፓርላማው ብዙ መቀመጫ ያላቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት ካቢላ ደጋፊዎችና ሀገሪቱን በመንግስትነት የሚያስተዳድረው የሺሴኬዲ ፓርቲ ፖለቲካዊ ልዩነታቸውን ማስታረቅ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡፡ […]