loading
በአምስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 በአምስት ወራት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ:: የንግድ ውድድሩን ፍትሀዊ ለማድረግና የፀረ-ኮንትሮባንድ እንቅስቃሴውን ለመቆጣጠር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ባደረጉት እንቅስቃሴ ነው እቃዎቹ የተያዙት፡፡ በዚህም ከሀምሌ እስከ ህዳር ባሉት አምስት ወራት ግምታዊ ዋጋቸው ከ1 ቢሊዮን 356 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የወጪና የገቢ […]

ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ ኮትዲቯርን ለሶስተኛ ጊዜ ለመምራት ቃለ መሃላ ፈፀሙ፡፡ በፈረንጆቹ ኦክቶበር 31 በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፕሬዚዳንት አላሳኒ ኦታራ 94 በመቶ በሆነ ድምፅ አሸንፈዋል መባሉን ተከትሎ ከረር ያለ ተቃውሞ ገጥሟቸው ነበር፡፡ ኦታራ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር የህገ መንግስ ማሻሻያ ሲያደርጉ ጀምሮ ነበር በሀገሪቱ ተቃውሞው የተቀሰቀሰው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ኦታራ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሏቸውን ተቃዋሚዎች […]

አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 06፣ 2013 አሜሪካ ከሩሲያ የሚሳኤል መከላከያ ሲስተም ገዝታለች በሚል ምክንያት በቱርክ ላይ ማዕቀብ ጣለች:: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ቱርክ ከሩሲያ የገዛችው የሚሳኤል መከላከያ ስርዓት ለአሜሪካ ደህንነት ስጋት መሆኑን ደጋግመን ነግረናት ነበር ብለዋል፡፡ ዋሽንግተን ያሳለፈችው ውሳኔ የቱርክን ወታራዊ አቅም የማዳከም ሳይሆን የራሷን ደህንነት የማስጠበቅ ነው በማለትም አክለዋል ፖምፒዮ፡፡ ቱርክ ባለፈው ጥቅምት ወር […]