loading
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸዉን ግዴታዎች ያላሟሉ ፓረቴዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ማሟላት የሚገባቸዉን ግዴታዎች ያላሟሉ ፓረቴዎች ላይ እርምጃ መዉሰዱን አስታዉቋል፡፡ በዚህም 26 ፓረቲዎች በቦርዱ ሚጠበቅባቸዉን ባለማሟላታቸዉ መሰረዛቸዉ ታዉቋል፡፡ ሁሉም ፓለቲካ ፓርቲዎች ማሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች በጽሁፍ እንዲደርሳቸው እንዲሁም ማምጣት ያለባቸውን ተጨማሪ የመስራች ፊርማ ቁጥር በመጥቀስ እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል፡፡ በዚህም መሰረት ማሟላት ያለባቸውን ሰነዶች ያላቀረቡ 26 ፓርቲዎች ተሰርዘዋል ብሏል :: […]

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአምስት ወር ዉስጥ ከ18 ሺህ በላይ የወንጀል መዛግብት ውሳኔ ሰጥቼያለሁ አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በአምስት ወር ዉስጥ ከ18 ሺህ በላይ የወንጀል መዛግብት ውሳኔ ሰጥቼያለሁ አለ፡፡ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ አወል ሱልጣን እንደገለጹት የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርዓቱን ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ፣ የፍትህ ስርዓትን በማስፈን እና ወንጀለኞችን ለህግ በማቅረብ ረገድ ተቋሙ በርካታ ስራዎችን መስራት ችሏል ብለዋል፡፡ በዚሁም መሰረት በአምስት ወር አፈጻጸም ውስጥ በሁሉም […]

እስራኤል በሁለት ዓመት ውስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ የግድ ሆኖባታል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 እስራኤል በሁለት ዓመት ውስጥ አራተኛ ምርጫ ማካሄዷ የግድ ሆኖባታል ተባለ:: የጠቅላይ ሚንስትር ቤናሚን ኔታኒያሁና የአጣማሪያቸው ቤኒ ጋንትዝ የአንድነት መንግስት በገጠመው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ድንገቴ ምርጫ የማካሄድ ግዴታ ውስጥ ገብቷል፡፡ ባለፉት ሳምንታት የሀገሪቱ ምክር ቤት ፈርሶ አዲስ ምርጫ ይካሄድ የሚል ሀሳብ በህግ አውጭ አባላት መቅረቡን ተከትሎ ፓርላማው ፈርሷል ነው የተባለው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ምርጫው […]

በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ መነሳቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ዳግም ተጀምሯል፡፡

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2013 በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል ተጥሎ የነበረው የጉዞ እገዳ መነሳቱን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎቱ ዳግም ተጀምሯል፡፡ በእንግሊዝ አዲሱ የኮሮናቫይረስ በመከሰቱ በርካታ ሀገራት የጉዞ እቀባ መጣላቸውን የሚታወስ ሲሆን ፈረንሳይም አንዷ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አሁን ላይ ሀገራቱ በደረሱት ስምምነት መሰረት በእንግሊዝና ፈረንሳይ መካከል የሚደረጉ የባቡር ፣የአየርና የባህር ጉዞዎች ዳግም እንደሚጀመሩ ነው የተነገረው፡፡ የፈረንሳይ ዜጎችና በፈረንሳይ የሚኖሩ የእንግሊዝ […]