የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባለፈው ሳምንት በ16 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገለፀ፡፡
አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣ 2013 የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ባለፈው ሳምንት በ16 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ገለፀ፡፡ ድርጅቱ ማክሰኞ አመሻሽ ላይ ባወጣው ሪፖርት ከኮቪድ 19 ጋር የተያያዘ የሞት መጠን መቀነሱንም አስታውሷል፡፡ ድርጅቱ ከስድስት የቁጥጥር ቀጠናዎች ከተላኩለት የበሽታው ስርጭት ሪፖርቶች መካከል በአምስቱ አዲሱ ቫይረስ በሁለት አሃዝ መቀነስ ሲያሳይ በሜዲትራኒያን አካባቢ ብቻ በ7 በመቶ ጭማሪ መመዝገቡ ታውቋል፡፡ […]