loading
አራት ተጠርጣሪዎች ከተሰረቁ የመኪና መለዋወጫዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2013 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለልማት በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ በተደረገ አሰሳ አራት ተጠርጣሪዎችን ከተሰረቁ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ክልል ልዩ ቦታ አሜሪካ ግቢ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው። መንግስት ለልማት ብሎ ባዘጋጀቸው ቦታዎች […]

አምብሮ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች ትጥቅ ማቅረብ የሚያስችለውን ስምምነት አራዘመ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣ 2013 አምብሮ የስፖርት ትጥቅ አምራች ኩባንያ ለኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሄራዊ ቡድኖች ትጥቅ ለማቅረብ የሚስችለውን ስምምነት ለአራት ዓመታት አራዘመ።አምብሮ ከፈረንጆቹ 2019 ጀምሮ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ይፋዊ የቴክኒካል ስፖንሰር በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። በአዲሱ ስምምነት መሰረትም አምብሮ ኩባንያ ለወንዶች ፣ ሴቶች ፣ ወጣቶች እና ለታዳጊ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኖች ሙሉ የጨዋታ […]

የ533 ሚሊየን ፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ በነፃ በበየነ መረብ ተለቀቀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2013 በመረጃ መረብ ጠላፊያዎች የፌስቡክ መረጃዎቻቸው ከተጠለፈባቸው 533 ሚሊየን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መካከል ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኢትዮጵያ መሰረታቸውን ያደረጉ የፌስቡክ አካውንቶች ናቸው ተብሏል። የመረጃ ጣለፊያዎች ከፌስቡክ የዘረፉት የግለሰቦች መረጃ በነፃ በጠላፊዎች ህዝባዊ ፎረም ላይ እንደሚገኝ ነው ብሌፒንግ ኮምፒዩተር የዘገው። ይህ የተሰረቀ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠላፊዎች ለአባላቱ መሸጥ […]

ኢዜማ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ችግር ያቃልላሉ ያላቸውን 138 ቁልፍ ግቦችን የያዘ የቃል ኪዳን ያለውን ሰነድ ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 ፓርቲው በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለመዲናዋ ነዋሪዎች ሊሰሩላቸው ይገባሉ ብሎ የለያቸውን 138 ቁልፍ ግቦች አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዳሉት ‘‘ኢዜማ እውነተኛ ፌዴራሊዝም መሰረቱ ያልተማከለ የአስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ነው’’፡፡አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ብትሆንም በቅድሚያ ለሚኖሩባት ዜጎች ምቹ ሆና እንድትገኝ ማድረግ ይገባናልም ብለዋል። “ፓርቲው ከሕዝቡ ጋር ወርዶ ባደረገው […]

የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሊጀምሩ ነው::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 የፖለቲካ ፓርቲዎች በመገናኛ ብዙኃን የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ሊጀምሩ ነው::ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ከነገ ጀምሮ በመገናኛ ብዙኃንማድረግ እንደሚችሉ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምረጡኝ ዘመቻቸው የሚጠቀሙበት ነፃ የአየር ሰዓት እና የጋዜጣ አምድ እጣ ድልድል መርሐ-ግብር ተከናውኗል፡፡ ድልድሉ 25 በመቶ ለፓርቲዎች በእኩል ክፍፍል የሚሰጥ ሲሆን፣ በስራ ላይ ባሉ […]

በአለም የመጀመሪያውን ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለመቆጣጠር የሚረዳ በጨጓራ ላይ የሚታሰር ቀለበት የፈለሰፉት ፕ/ር ምትኩ በላቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ::

በአለም የመጀመሪያውን ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለመቆጣጠር የሚረዳ በጨጓራ ላይ የሚታሰር ቀለበት የፈለሰፉት ፕ/ር ምትኩ በላቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ::ታዋቂው የቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ፕሮፌሰር ምትኩ በላቸው በምእራብ ሸዋ ወንጪ የተወለዱ ሲሆን እድሚያቸዉ 12 አመት ሲሞላ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል፡፡ ፕ/ር ምትኩ ትምህርታቸዉን ሲከታተሉ ከነበረበት የአሁኑ አዲስ […]

አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ:: አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ሁሉ ምቹ ከተማ ለማድረግ የተለያዩ የልማት ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ። የከተማ አስተዳደሩ የአርሶ አደር መንደሮችን ተዳራሽ ማድረግ የሚያስችሉ የመንገድ ስራፕሮጀክቶችን አስጀምሯል። የከተማ መስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ […]

በቻድ ምርጫው እንዲደናቀፍ ቢደረግም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደተሳተፈ ገዥው ፓርቲ ተናገረ ፡፡

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 በቻድ ምርጫው እንዲደናቀፍ ቢደረግም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ እንደተሳተፈ ገዥው ፓርቲ ተናገረ ፡፡ በቻድ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መራጮች እንዳይሳተፉ በተቃዋሚዎች ጥሪ የቀረበላቸው ቢሆንም የድምፅ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ የተካሄደ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል ፡፡ እሁድ እለት የተካሄደውን የምርጫ ውጤትም ቻዳውያን እየተጠባበቁ ሲሆን የወቅቱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ሁነኛ ተቀናቃኞች ሳይገጥሟቸው ከሰባቱ […]

ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለዉ አንድ ሰዉ በፖሊሶች በግፍ ከተገደለ በኋላ በሚኒያ ፖሊስ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀጣጠሉ፡፡

አዲስ አበባ፣  ሚያዚያ ፡ 04፣ 2013 ጥቁር ቆዳ ቀለም ያለዉ አንድ ሰዉ በፖሊሶች በግፍ ከተገደለ በኋላ በሚኒያ ፖሊስ አቅራቢያ የተቃውሞ ሰልፎች ተቀጣጠሉ፡፡ በአሜሪካ ብሩክሊን ማእከል ውስጥ የትራፊክ ማቆሚያ አካባቢ ፖሊሶች ጥቁር ቀለም ያለዉን አንድ ሰዉ በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተኩሰው ከገደሉ በኋላ የተቃውሞ ሰልፎች በሚኒያፖሊስ አቅራቢያ መካሄዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሟች ዱዋንት ራይት የ20 ዓመት ወጣት መሆኑን […]

ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013 ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እንደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሊከናወን ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቀርተውታል ያሉ ሲሆን፤ በሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 38 ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንደሚደነግግ ገልጸዋል። የሀገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ካርድ […]