loading
የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ የከፈቱት መንግሥት ለነሱ ጥቅም ባለመቆሙ ነው- የህግ መምህርና የማህበረሰብ አንቂ ሙክታር ኡስማን::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 አንዳንድ የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ ዘመቻ የከፈቱት አሁን ኢትዮጵያን እየመራ ያለው መንግሥት አሸባሪው ህወሓት ስልጣን ላይ እያለ እንደነበረው ለነሱ ጥቅም የቆመ ባለመሆኑ እንደሆነ የህግ መምህርና የማህበረሰብ አንቂው አቶ ሙክታር ኡስማን ተናገሩ። አቶ ሙክታር ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ አሁን ስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት በራሱ የሚተማመንና እና በምሥራቅ አፍሪካ ለውጥ ለማምጣት መሥራት […]

ባላመንበት ጦርነት የገባነው ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው- የሕወሓት ምርኮኞች ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባና አፈና በዝቶብን ተሰቃይተን ነው::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 ባላመንበት ጦርነት የገባነው ድብደባ በዝቶብን ተሰቃይተን ነው- የሕወሓት ምርኮኞች ባላመንበት ጦርነት የገባነው እምቢ በማለታችን ድብደባና አፈና በዝቶብን ተሰቃይተን ነው በአፋር ግንባር ተሰልፈው የነበሩ የሕወሓት ምርኮኞች ተናገሩ። ካልአይ መምበረ በፈንቲ – ረሱ ግንባር በተካሄደው ውግያ ቆስሎ የተማረከ ሲሆን ከመቀሌ ከተማ ድንገት ታፍኖ ከታሰረ በኋላ የሦስት ቀናት ስልጠና ከተሰጣቸው መካከል አንዱ በመሆን […]

ለመጀመሪያ ጊዜ በበይነ መረብ ለማስተማር ለ4 ተቋማት ፈቃድ ተሰጠ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013  በበይነ መረብ (ኦንላይን) ትምህርት ለመጀመር ካመለከቱ 9 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ ለ4 ተቋማት የእውቅና ፈቃድ መስጠቱን የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አስታወቀ። በዚህም አራቱ ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪና በሁለተኛ ዲግሪ በ6 ፕሮግራሞች የእውቅና ፈቃድ እንደተሰጣቸው ነው የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ገረሱ ለኢቲቪ የገለጹት። በበይነ መረብ (ኦንላይን) ለማስተማር ፈቃድ […]

አሸባሪውን የሕወሓትን ኃይል ከታሪክ ገጽ ለመደምሰስ ጊዜው አሁን ነዉ -የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2013 ሀገር በመከላከል ዘመቻው ለመሳተፍ እድሜያችሁና ዐቅማችሁ የሚፈቅድላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የመከላከያ ሠራዊቱን እንዲቀላቀል ጥሪ ቀረበ፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ባደረገዉ ጥሪ ፣ዐቅማችሁ የሚፈቅድላችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የመከላከያ ሠራዊቱን ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻውን በመቀላቀል የሀገር ዘብነታችሁን የምታሳዩበት ትክክለኛው ጊዜ አሁን ነው ብሏል፡፡ አሸባሪውን የሕወሓት ኃይል ከታሪክ ገጽ ለመደምሰስ የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን፣ የክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች፣ […]