loading
ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ በኮቪድ- 19 ምክንያት 20 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 ባለፉት ሁለት ቀናት በኢትዮጵያ በኮቪድ- 19 ምክንያት 20 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ፡፡የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓታት የኮቪድ-19 መረጃ እንደሚያመለክተው በተከታታይ በሁለት ቀናትውስጥ 20 ሰዎች ህይወታቸውን በቫይረሱ አጥተዋል፡፡ ቫይረሱ ሀገራችን ከገባ ጀምሮም ህይወታቸው በቫይረሱ ያለፈ ሰዎች ቁጥር 4 ሺህ 4 መቶ 50 ደርሷል፡፡የጽኑ ህሙማንም ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን ፤ የ24 ሰዓታቱ ሪፖርት […]

የህወሓት ሽብር ቡድን እና የተላላኪዎቹ እቅድ በህዝቦች ህብረት ዛሬም ይከሽፋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 የህወሓት ሽብር ቡድን እና የተላላኪዎቹ እቅድ በህዝቦች ህብረት ዛሬም ይከሽፋል- አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሽብር ቡድኑ ህወሓት እና የተላላኪዎቹ እቅድ በህዝቦች ህብረት ዛሬም እንደሚከሽፍ ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ በህወሓት እና በተላላኪዎቹ የምትፈርስ ሳትሆን በህዝቦቿ አንድነት ተገንብታ […]

አሸባሪው ህወሓትን ከመቃብር ለማንሳት የሚጥሩትን መመከት ይገባል- ባልደራስ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013  ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያን አሁን ላለችበት ሁኔታ የዳረጋትን ሥርዓት ከመቃብር ለማንሳት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በተባበረ ክንድ መመከት እንደሚገባ ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ገለጸ፡፡ የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ዶክተር በቃሉ አጥናፉ ትህነግ የአክራሪ ብሄርተኝነት የመጨረሻው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ የመንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ መልካም ቢሆንም አሸባሪው ህወሓት ትንኮሳውን አለማቆሙ ለሠላም ቅንጣት ታህል ፍላጎት […]

በኬኒያ የኮቪድ-19 ክትባት የማይከተቡ የመንግስት ሰራተኞች ቅጣት ይጠብቃቸዋል::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013  በኬንያ የመንግሥት ሠራተኞች በሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት እንዲከተቡ የ13 ቀናት ጊዜ ተሰጣቸው ፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ የማይከተቡ የመንግሥት ሠራተኞች የዲሲፕሊን እርምጃ ይጠብቃቸዋል መባሉን አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡ የመንግሥት ሠራተኞች ሃላፊው ጆሴፍ ኪንዩዋ አንዳሉት ከሆነ ውሳኔው የተላለፈው በተለይ በመምህራንና በፀጥታ ዘርፍ ውስጥ ባሉ የመንግሥት ሠራተኞች አካባቢ የኮቪድ-19 ክትባት የመከተብ ዝንባሌ ዝቅተኛ በመሆኑ […]