loading
ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም ድጋፍ ጠየቀች::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 ጣሊያን የገጠማትን ሰደድ እሳት ለመቋቋም የአውሮፓ ህብረትን ድጋፍ ጠየቀች፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ከአሁን ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ብለው የጠሩት የእሳት አደጋ በአስር ሺዎች ሄክታር የሚለካ መሬት መሸፈኑ ተነግሯል፡፡ የእሳት አደጋው የደረሰው ሳርዲኒያ በተባለች ደሴት ሲሆን በርካታ የደሴቷ ነዋሪዎች ራሳቸውን ከአደጋው ለማዳን መኖሪያ አካባቢዎቻቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡ ፈረንሳይና ግሪክ የጣሊያን መንግስት ያቀረበውን የድጋፍ […]

ሞት አፋፍ ላይ የሚገኘው ህወሃት ህጻናትን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ መጠቀሙን ቀጥሏል ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 21፣ 2013  አሸባሪው ህወሃት በአፋር ክልል ፈንተ-ረሱ በከፈተው ጥቃት አሁንም ህጻናትን እንደ ሰብዓዊ ጋሻ እየተጠቀመ ይገኛል። የሃገር መከላከያ ሠራዊትና የክልሉ ልዩ ሃይል በግንባሩ እየወሰዱት ባለዉ እርምጃ ጅንታዉን ከአካባቢዉ የማጽዳት ዘመቻ ተጨማሪ ለውጊያ ያልደረሱ ታዳጊዎች ተይዘዋል።  በግንባሩ ህብረሰተቡን በማስተባበር ስራ ላይ የሚገኘዉ የክልሉ ማረሚያ ቤት ምክትል ኮሚሺነር አቶ መሀመድ አህመድ ለኢዜአ እንደተናገሩት […]

መንግስት 41ሺህ 485 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ መመለሱን ገለጸ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 21፣ 2013  የኢትዮጵያ መንግስት 80 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 41ሺህ 485 ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ እንዲመለሱ ማድረጉን የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አማካኝነት በአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ምላሽ ማእከል ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ወገኖችን በመቀበል እና በማስተናገድ እንዲሁም ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ በማድረግ እየሰራ እንደሆነ የኮሚሽኑ […]

ኢዜማ ያቀረበዉ የይግባኝ አቤቱታ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ኢዜማ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ ተቀበለ፡፡ ፍርድቤቱ አቤቱታዉን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ይዞ እንዲቀርብ ለሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ቀጠሮ እንደሰጠዉ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ ) በማህበራዊ ገጹ አስታዉቋል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኢዜማ በ28 ምርጫ […]

ለህዳሴ ግድብ ከዳያስፖራው የተሰበሰበ ገንዘብ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 ለህዳሴ ግድብ በዚህ ዓመት ከ134 ሚሊዮን ብር በላይ ከዳያስፖራው ተሰበሰበ:: የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪ ብሔራዊ ምክርቤት ጽ/ቤት እንዳስታወቀዉ  ላለፉት 10 ዓመታት ዳያስፖራው በቦንድ ግዢ እና በስጦታ ያደረገው ድጋፍ ከ 1 ነጥብ 5 በሊዮን ብር በላይ ነዉ፡፡ የውሃ ሙሌትተከትሎ በተፈጠረው መነሳሳት ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ከፍተኛ ድጋፍ እየተደረገ  ነው፡፡ከዚህ […]

ስምንት የግብጽ ወታደሮች በፀረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ ላይ ሳሉ መገደላቸው ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 26፣ 2013 ስምንት የግብጽ ወታደሮች በፀረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ ላይ ሳሉ መገደላቸው ተገለፀ፡፡ ስምንቱ ግብጻውያን ወታደሮች በጸረ ሽብርተኝነት ተልዕኮ በነበሩበት መገደላቸውን የጦሩ ቃል አቀባይ ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ እንደ ወታደራዊ ሃይሉ መግለጫ በአብዛኛው ውጊያው እየተካሄደ የነበረው የታጠቁ የዳኢሽ ቡድኖች በሚንቀሳቀሱበት ሰሜናዊ ሲናይ በረሃ ላይ እንደነበር ተገልጿል፡፡ ወታደሮቹ በሙሉ እዚያ ይሁን በሌላ ስፍራ ስለመሞታቸው ግን […]

ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ገንቢ ሀሳቦችን አንስተዋል::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 የዩ ኤስ ኤድ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ገንቢ ሀሳቦች ማንሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምበሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ሳማንታ ፓወር በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ገንቢ ሀሳቦች ማንሳታቸውን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል መንግስት እየሰራቸው ያሉ የሰብዓዊ እርዳታ ስራዎችን ከሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ […]

ዩ ኤስ ኤድ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አደረገ::

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 29፣ 2013 ዩ ኤስ ኤድ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ይፋ አደረገ:: ዩ ኤስ ኤድ የተሰኘው የአሜሪካ ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት ለኮቪድ 19 ምላሽ እና ማገገሚያ የሚውል 720 ሚሊዮን ዶላር ማፅደቁ ተሰማ፡፡ የአሜሪካ ዓለምአቀፍ ተራድኦ ድርጅት ኃላፊ ሳማንታ ፓወር እንደገለፁት በጀቱ የኮቪድ 19 ስርጭትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመግታት ያለመ […]

የወልድያ ከተማ ነዋሪዎች የመንግሥትን አፋጣኝ እርምጃ ጠየቁ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 የህዋሓት ቡድን ነሀሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽቱን ወደ ወልድያ ከተማ በተደጋጋሚ ከባድ መሣሪያ መወርወሩን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል፡፡ ነዋሪዎቹ መንግሥት በህዋሓት ቡድን ላይ የአካባቢውን ሕዝብ የትግል ጥንካሬ በመጠቀም ፈጣን እርምጃ መውሰድ ባለመቻሉ የሽብር ቡድኑ ከተማዋን ለማውደም ኃላፊነት በጎደለው መልኩ ከባድ መሣሪያ መወርወር ጀምሯል ብለዋል። መንግሥት […]

አልማ ማህበር የህወሓት ቡድን በፈጠረ ቀውስ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የዕለት ደራሽ ድጋፍ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 3፣ 2013 የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አራጋው ታደሰ እንደገለፁት በዋግ ህምራና ሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የቆቦ፣ ራያ አላማጣና ግዳን ወረዳ ነዋሪዎች በአሸባሪው ትህነግ ምክንያት ከሰላማዊ ኑሯቸው ተፈናቅለው ደሴና ወልድያ ከተማ ለሚገኙ የዕለት ደራሽ ድጋፍ አቅርበዋል። ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን እንደ አስፈላጊነቱ መፈፀም በሚያስችለው ስትራቴጅያዊ የለውጥ ዕቅድ መሰረት ቡድኑ በፈጠረው ቀውስ […]