loading
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺህ የሚደርሱ ህፃናት ከእግር መቆልመም ችግር ጋር ይወለዳሉ ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺህ የሚደርሱ ህፃናት ከእግር መቆልመም ችግር ጋር ይወለዳሉ ተባለ፡፡ ይሁን እንጂ የህክምና አገልግሎቱን ከሚፈልጉት የችግሩ ተጠቂ ህጻናት መካከል 50 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን የጤና ሚስቴር ገልጿል፡፡ በሚኒስቴሩ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር አባስ ሀሰን ችግሩ ያለባቸውን ህጻናት በጊዜ መለየትና ፈጥኖ ማከም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ለሙያተኞች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የጤና […]

የግብርና ሚኒስቴር  በሰው ሰራሽ ዘዴ ሴት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 የግብርና ሚኒስቴር  በሰው ሰራሽ ዘዴ ሴት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊያደርግ ነው፡፡ ፕሮጀክቱን በይርጋለም ከተማ በይፋ ያስጀመሩት የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ የወተት ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ  ነው ብለዋል።በሀገሪቱ በተመረጡ 58 ወረዳዎች ከዓለም ባንክ በተገኘ 176 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በወተት ላም፣ በዶሮ፣ በዓሣና በስጋ ከብት ላይ […]

በቻይና 132 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበር ቦይንግ 737 አውፕላን መከስከሱ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 በቻይና 132 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበር ቦይንግ 737 አውፕላን መከስከሱ ተሰማ፡፡ የምስራቅ ቻይና አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላኑ ጉዋንግዚ በተባለች ግዛት የተከሰከሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እተጣራ ነው ተብሏል፡፡ አደጋው የተከሰተው አውሮፕላኑ መንገደኞችን ከኩሚንግ ወደ ጉዋንግዙ ከተማ በሚያጓጓጉዝበት ወቅት መሆኑን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡ አልጀዚራ ከቻይና ባሰራጨው ዘገባ ሀገሪቱ በዓመት […]