loading
የኢትዮጵያ መንግስት የግጭት ማቆም እርምጃ በምዕራባዊን ዓይን…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት ለማቆም መወሰኑን አሜሪካና አውሮፓ ህብረት አደነቁ:: የአውሮፓ ህብረት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ መንግስት የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ መዘጋጀቱን ነው የገለጸው፡፡ ህብረቱ አክሎም ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አካላት ጋር በመተባበር ድጋፉ በፍጥነት እንዲደርስ እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡ በሌላ በኩል ከመንግስት በኩል እንደተደረገው ሁሉ […]

ስራውን ቆጥሮ ያስረከበው ምክር ቤት ውጤቱን በአግባቡ ቆጥሮ ይረከብ ይሆን?

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 የአዲስ አበባ ምክር ቤት ቆጥሮ የሰጠውን ስራ ቆጥሮ መረከብ የሚያስችለውን የፊርማ ስነስርዓት አከናወነ፡፡ ምክር ቤቱ አስፈፃሚውን የመከታተልና መቆጣጠር ስልጣን ተግባራዊ ለማድረግ ብሎም የተጠያቂነትን ስርዓት ለማስፈን ይረዳው ዘንድ ነው ይህን ያደረገው፡፡ ሥምምነቱ በዋናነት በምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና በአስፈፃሚዎች (የቢሮ ሃላፊዎች) መካከል የተቋማቱን እቅድ መሰረት ያደረገ ይዘት ያለው ሲሆን ከንቲባ አዳነች አቤቤ […]

በሶማሊያ በተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶች የ48 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2014 በሶማሊያ በተፈፀሙ ሁለት የሽብር ጥቃቶች የ48 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ በማዕከላዊ ሶማሊያ በተፈፀሙት ጥቃቶች የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 48 ከፍ ያለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የሂርሻቤል ግዛት አስተዳዳሪ የአልሸባብ አማፂያን ከምርጫው በፊት ፖለቲከኞች ላይ ማነጣጠራቸውንአስታውቀዋል። መጀመርያ በሂርሻቤል ቤልደዌን አውራጃ በተፈፀመው የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃት አሚና መሀመድ አብዲን ጨምሮ ሁለት የአካባቢው ህግ አውጪዎች […]