loading
የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ለህብረተሰቡ መድረሳቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት እንደሚገባ ምክር ቤቱ አሳሰበ።

የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ከውጭ የሚገቡ ሸቀጦች ለህብረተሰቡ መድረሳቸውን የሚያረጋግጥ ጠንካራ የቁጥጥር ስርአት መዘርጋት እንደሚገባ ምክር ቤቱ አሳሰበ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 5ኛ መደበኛ ስብሰባ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴርን የ8 ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ሲገመግም በኑሮ ውድናትና ህገ-ወጥነት ላይ ትኩረት አድርጎ ተወያይቷል። ሚኒስትሩ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በወጪ ንግድ ገቢ፣ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች አቅርቦትና ስርጭት፣ እንዲሁም የአሰራር […]

የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱ የተፈረመው በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መካከል ነው፡፡ ይህ ስምምነት የተናበበና የተቀናጀ የአሠራር ሥዓርት በመዘርጋት የሀብትና የጊዜ ብክነትን በማስቀረት ብቁ የሰው ኃይል በማፍራት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሚተገበሩ ፕሮግራሞች ላይ እንዲሳተፉ ያግዛል ነው የተባለው፡፡ […]

የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዳርፉር ያለውን የክስ ሁኔታ መቋጫ ማበጀት እፈልጋለሁ አሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በዳርፉር ያለውን የክስ ሁኔታ መቋጫ ማበጀት እፈልጋለሁ አሉ፡፡የፍርድ ቤቱ ዋና አቃቤ ህግ ካሪም ካህን በሄግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር በቅርቡ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ወይ ተብለው ሲጠየቁ በዳርፉር ያለውን ሁኔታ መዝጋት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል ተብሏል። የቀድሞ የሱዳን ሚሊሻ ሃላፊ አሊ […]