loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅመ ደካሞች በቤተ-መንግሥት ማዕድ አጋሩ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅመ ደካሞች በቤተ-መንግሥት ማዕድ አጋሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ጧሪ ለሌላቸው አረጋዊያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በተለያዩ ምክንያቶች ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ህፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው በድምሩ 230 ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ወገኖች በቤተ-መንግሥት ተገኝተን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተደረገልን ግብዣና መልካም መስተንግዶ እናመሰግናለን ብለዋል። ማዕድ ተጋሪዎቹ […]

የጥቁር አንበሳ የልብ ሕክምና ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 የጥቁር አንበሳ የልብ ሕክምና ማዕከል የማስፋፊያ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተጠናቆ ሥራ ጀመረ፡፡ በዛሬው ዕለት የተመረቀው የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ የተለያዩ የሕክምና ግብዓቶች እንደተሟሉለት ተነግሯል። ለአብነትም በአፍሪካ ብቸኛው ልብ ሳይከፈት ቀዶ ህክምና ማድረግ የሚያስችል መሣሪያ ተበርክቶለታል ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ለፕሮጀክቱ 39 ነጥብ 720 ሚሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግበት ሲሆን ወጪውም 50 በመቶው በኔዘርላንድስ መንግሥት […]

ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አደረገ። የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎችምደባ ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ […]