loading
አዲሱ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ መሆን…

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 በቅርቡ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያን ተከትሎ የትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገለጸ፡፡ በዚህም መሰረት በሚኒ ባስ እና በሚዲ ባስ ተሸከርካሪዎች ከ50 ሳንቲም እስከ 3 ብር ከ50 ሳንቲም ጭማሪ ስለመደረጉ ተነግሯል፡፡ ጭማሪው ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ከታሪፍ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ አገልገሎት ሰጭዎች ካጋጠሙ ማህበረሰቡ ለሚመለከተው አካል […]

የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 የመመስረቻ መስፈርት አሟልተው የተገኙ ስምንት አዳዲስ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ተሰጣቸው፡፡በፋይናንስ ዘርፉ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ ለውጦችን ተከትሎ በርካታ ባንኮች የመመስረቻ ፈቃድ ለማግኘት ጥያቄ እያቀረቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የባንክ ቁጥጥር ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው ባንክ ለመመስረት የሚያስፈልገው ዝቅተኛ የካፒል መጠን ከ500 ሚሊዮን ወደ 5 ቢሊዮን ብር ከፍ መደረጉን አስታውሰው […]

ሞሳድ የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል አሲሯል-የኢራን የስለላ ምንጮች

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2014 እስራኤል የኢራኑን ፕሬዚዳንት ለመግደል ማቀዷን ደርሸበታለሁ ሲል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አስታወቀ፡፡ ቴልአቪቭ ይህን የምታርገው በኢራን መረጋጋት እንዳይፈጠር ለማድረግ መሆኑንም አብዮታዊ ዘቡ አብራርቷል፡፡ ተቋሙ በይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ባሰፈረው ጽሁፍ የእስራኤሉ የስለላ ድርጅት ሞሳድ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከቴህራን ውጭ በሚገኙበት ወቅት ግድያው እንዲፈጸምባቸው እቅድ መንደፉን የደህንነት መረጃ ያላቸው ምንጮች ነግረውኛል […]