loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር በሀገራዊና ቀጠናዊ ዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያና ጣሊያን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ የጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ምሽት አዲስ አበባ […]

ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ካፒታል ስራውን የሚጀምረው አማራ ባንክ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 አማራ ባንክ አክሲዮን ማህበር በሳምንቱ መጨረሻ ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ይፋ አደረገ፡፡ ባንኩ በ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መነሻ ካፒታል ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ስራውን በይፋ እንደሚጀምር ነው ያስታወቀው፡፡ የባንኩን ስራ የመጀመር ሂደትን አስመልክቶ የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ጋዜጣዊ ሰጥተዋል። በ6 ቢሊዮን 516 ሚሊዮን ብር በላይ በተከፈለ የመነሻ […]

ሞስኮን ያልበረገራት የምእራባዊያን የነዳጅ ማእቀብ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 በሩሲያ ላይ የተጣለው የነዳጅ ግብይት ማእቀብ ግቡን እዳልመታ የሚገልጽ አዲስ ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡ ሪፖርቱ ፕሬዚዳንት ቭላደሚር ፑቲን ጦራቸውን ወደ ዩክሬን ባዘመቱ በ100 ቀናት ውስጥ ሞስኮ ከነዳጅ ሽያጭ 98 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቷን ይገልጻል፡፡ ይህን ሪፖርት ይፋ ያደረገው ተቀማጭነቱ ፊንላንድ የሆነ በኢነርጂና ንጹህ አየር ላይ ምርምር የሚያደርግ ገለልተኛ ተቋም ነው […]