loading
የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪው የሸኔ ቡድን በምዕራብ ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ ያደረሰውን አደጋ በፅኑ አወገዘ፡፡ ምክር ቤቱ የሽብር ቡድኑ በጸጥታ ሀይሎች ጥቃት እየደረሰበት በመሆኑ ከጥቃቱ በመሸሽ በምዕራብ ወለጋ ንጹሀን ዜጎች ላይ አደጋ አድርሷል ብሏል። በኦሮሚያ ክልል፣ ቄለም ወለጋ ዞን የሚገኙ ንጹሀን ዜጎቻችን ላይ የፈጸመው ጭፍጨፋ በእጅጉ የሚወገዝ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በዜጎቻችን […]

የመንግስት ህግ የማስከበር ሀላፊነት ጥያቄ ውስጥ መግባቱ አሳስቦኛል -ኢዜማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ኢዜማ ፓርቲ መንግስት የህግ የበላይነትን የማስከበር ሃላፊነቱ ከዕለት ዕለት ጥያቄ ውስጥ እየገባ መምጣቱ በብርቱ አስግቶኛል አለ።ፓርቲው ይህን ያለው በቄለም ወለጋ በንጹሀን ዜጎች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግድያ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው፡፡ ኢዜማ “በድንገት መጥቶ ህዝብን ከሚያጠቃው እኩይ አካል እኩል ዜጋውን የመጠበቅ ግዴታ ኖሮበት የማይጠብቀው መንግስት ተጠያቂ ነው” […]

የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 የሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት መሪ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጦር ሰራዊቱ ከመንግስት አስተዳዳሪነቱ እንደሚነሳ አስታወቁ፡፡በመፈንቅለ መንግስት የመሪነቱን ስፍራ የያዙት አል ቡርሃን ጦሩ ከፖለቲካዊ ውይይቶች ራሱን እንደሚያግል ያስታወቁ ሲሆን የሲቪል የሽግግር መንግስት እንዲመሰርቱ እንደሚፈቅድ ገልፀዋል። የጄኔራሉ መግለጫ የተሰማው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ አገዛዝ እንዲያበቃ የሚጠይቁ መጠነ ሰፊ ህዝባዊ ተቃውሞዎች መቀጠላቸውን ተከትሎ […]