loading
በልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጦች እና የፅዳት ዕቃዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉት ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 በልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጦች እና የፅዳት ዕቃዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉት ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡ ህገ-ወጦች ላይ እየተደረገ ያለው ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽኑ አስታወቋል፡፡ በአዲስ አበባ የኮረና ቫይረሰ መከሰቱን ምክንያት በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦችና የንግድ ተቋማት በፊት መሸፈኛ ማስክ ፣ በፅዳት ዕቃዎች […]

ቤጂንግ ሮምን አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እያለቻት ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 ቤጂንግ ሮምን አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እያለቻት ነው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂምፒንግ ከጣሊያኑ ጠቅላይ ሚስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ጣሊያን ቫይረሱን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት በሚገባ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ጣሊያን እና ቻይና ተመሳሳይ ፈተና ገጥሟቸዋል ያሉት ፕሬዝዳንት ሺ፣ ቻይና ቫይረሹን በመከላከሉ ረገድ ተሳክቶላታል ወረርሽኙን ለማጥፋት ከሌሎቹ ሀገራት ጋር ተባበረን  እንሰራለን ብለዋል፡፡ […]

የሁሉም የተፋሰሱ አባል አገራት በአባይ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ገለጹ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 የሁሉም የተፋሰሱ አባል አገራት በአባይ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም እውቅና ሊሰጠው ይገባል ሲሉ ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ገለጹ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት  ሣህለ ወርቅ ዘውዴ  ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት  ፖል ካጋሜ ጋር በኪጋሊ ተገናኝተው በሁለትዮሽና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ተነጋግረዋል፡፡ ፕሬዝደንት ፓል ካጋሜ በዚህ ወቅት ባደረገት ንግግር በአባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል የሚደረገው የትብብር እንቅስቃሴ ከሁሉ በፊት […]

ቦርዱ የመራጮች ትምህርት ማስተማር ለሚፈልጉ ሲቪል ማህበራት የእውቅና ፍቃድ የመስጫ ግዜን አራዘመ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 ቦርዱ የመራጮች ትምህርት ማስተማር ለሚፈልጉ ሲቪል ማህበራት የእውቅና ፍቃድ የመስጫ ግዜን አራዘመ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዳስታወቀዉ ለመራጮች ትምህርት ማስተማር ለሚፈልጉ ሲቪል ማህበራት   ለቦረድ ማመልከቻዎችን ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ የሚጠናቀቀው መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓ.ም እንደነበረ አስታዉሶ፡፡ ነገር ግን ቦርዱ ተጨማሪ የምዝገባ ቀናት አስፈላጊነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት የማመልከቻ ማስገቢያው የጊዜ ገደብ […]

የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ::

የአለም ባንክ ለአገራት የገንዘብ ድጋፍ ፈቀደ:: የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ቦርዶች ለሀገራት እና ኩባንያዎች ለለኮቪድ -19 መስፋፋት ለመከላከል ፣ ለመለየት እና ምላሽ ለመስጠት በሚያደርጉት ጥረት 14 ቢሊዮን ዶላር ለፈጣን ቁጥጥር ፋሲሊቲ እንዲጨምር ፈቀደ ፡፡በሳምንቱ መጨረሻ የዓለም ባንክ ለፈጣን ቁጥጥር 1ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በ 40 አገሮች ውስጥ ፕሮጀክቶችን እያዘጋጀ ነውም ተብሏል፡፡ በአፍጋኒስታን እና […]

በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ::

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2012 በኬንያ በዓለም አቀፍ ተቋሞች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ:: በናይሮቢ በተባበሩት መንግስታትና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ማህበር (በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ መግለጻቸዉን በኬኒያ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡ የማህበሩ አባላት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ከመከሩ በኋላ ባወጡት የጋራ አቋም መንግስት […]

የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012 የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥ የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት አስታወቀየኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ጽ/ቤትም የበጀት ዓመቱ ለመጠናቀቅ በሚቀሩት ሶስት ወራት ውስጥ ለሚኖሩት ሥራዎች የሚያስፈልገውን ወጪ በማብቃቃትና በቁጠባ በመጠቀም ከተመደበለት መደበኛ በጀት የሚቀነስ የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለዚህ ሀገራዊ ጥሪ እንደሚሰጥም  አስታውቋል ፡፡ከዚህ በተጨማሪም  ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመስጠት መወሰናቸው   የፕሬዝዳነት […]

በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012  በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት:: ኮቪድ 19 በአፍሪካ መዛመቱን ቀጥሏል፤ በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 200 በላይ ከፍ ብሏልየሀገሪቱ መንግስት ይፋ ባወጣው መረጃ በደቡብ አፍሪካ በበሽታው የተያዙ ሰዎች 1 ሺህ 280 ደርሷል ነው የተባለው፡፡ደቡብ አፍሪካ ሁለኛውን ሞት ይፋ ያደረገች ሲሆን በቫይረሱ ከተያዙት መካከል 31 የሚሆኑትን አክማ ማዳኗንም ተናግራለች፡፡የበሽታው […]

ፖፕ ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያስተላለፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012  ፖፕ ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያስተላለፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለዓለም ያስተላፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉት ተናግረው በዚም ዓለም በሙሉ አቅሟ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እንድትከላከል ያስችላታል ብለዋል፡፡ በዓለም እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ  በሚደረግ ጥረት ላይ ከፍተኛ […]

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ  ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት  ሰዎች መገኝታቸው ተረጋግጧል፡፡በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስት ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውም ታዉቋል፡፡የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ […]