loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እስከ 75 ሺህ ወታደሮችን በሁሉም የአሜሪካ ከተሞች ለማሰማራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ ይህን የምናደርገው ከየግዛቶቹ የድጋፍ ጥያቄ ከቀረበልን ነው ያሉት ትራምፕ አግዙን የሚሉን ከሆነ ያለማቅማማት እናደርገዋለን ብለዋል፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ […]

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ኢትዮጵያ እና ጃፓን የ490 ሚሊየን ብር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ::ስምምነቱን የኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ማትሱናጋ ዳይሱኬ ተፈራርመውታል፡፡ ገንዘቡ በኢትዮጵያ ኪቪድ19ኝን ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለህክምና ቁሳቁስ መግዣ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ሁለቱን የከተማ አስተዳደሮች ጨምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ሆስፒታሎች ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በማቅረብ የጤና ስርአቱን ለማዘመን ለሚደረገው […]

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ሊፈጠር የሚችል ተገቢነት የሌለው የዋጋ ግሽበትን ለመከላከልና የምርት እጥረት እንዳይከሰት በተሰራ የተቀናጀ ስራ ከክልል አምራች ኅብረት ሥራ ማኅበራት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡ ከተሰበሰበው ምርት ውስጥ ከ875 ሺህ […]

ሱዳን ወሳኙ የህዳሴው ግድብ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ20፣ 2012 ሱዳን ወሳኙ የህዳሴው ግድብ ድርድር እንዲቀጥል ጥሪ አቀረበች::የሱዳን የመስኖና የውኃ ሀብት ሚኒስቴር ቀጣዩ ወሳኝ ድርድር ቁርጥ ያለ ጊዜ ተይዞለት ግልፅ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ አተኩሮ እደካሄድ የሚል ጥሪ አቅርቧል፡፡ሚኒስቴሩ በመግለጫው ድርድሩ የሁሉንም ወገኖች ጥቅም የሚያስጠብቀና ከሚታወቁት አጀንዳዎች ውጭ የሆኑ ሀሳቦች ሳይካተትበት ወደ ውይይቱ መግባተ ያስፈጋል ሲልም አሳስቧል፡፡ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው ካርቱም ባለፈው […]

የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ በማሊ የአንድነት መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ21፣ 2012 የምዕራብ አፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ በማሊ የአንድነት መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ:: የቀጠናው ሀገራት መሪዎች በማሊ እየተባባሰ ለመጣው የአለመረጋጋት ችግር መፍትሄ ለማፈላለግ የሚያደርጉት ጥረት እስካሁን ይህ ነው የሚባል ውጤት እንዳላስመዘገበ ይነገራል፡፡ሰሞኑን ያደረጉት ስብሰባም በሀገሪቱ ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ የገቡትን ወገኖች ማስማማት አቅቷቸው ውይይታቸው ያለውጤት ነበር የተበተነው፡፡ አልጀዚራ እደዘገበው ኢኮዋስ በተቃራኒ ጎራ የቆሙት ወገኖች […]

የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጅብ ራዛቅ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ21፣ 2012 የቀድሞው የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጅብ ራዛቅ በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተባሉ:: እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2009 እስከ 2018 ማሌዢያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ናጅብ በሰባት ክሶች ነው ጥፋተኛ ሆነው የተገኙት፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው ናጅብ የቀረቡባቸውን ክሶች በሙሉ አልፈፀምኩም በማለት ቢቃወሙም አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን ክስ በማስረጃ በማረጋገጡ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 10 ሚሊዮን ዶላር የመንግስት […]

ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ሂዝቦላ በእሳት እየተጫወተ ነው ሲሉ አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ 22፣ 2012 እስራኤል ሰሞኑን በድንበር አካባቢ ከሂዝቦላ ታጣቂዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ማድረጓንና የተቃጣባትን ጥቃት በብቃት መመለሷን ተናግራለች፡፡ኔታኒያሁ በሰጡት መግለጫ የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ሉዓላዊ ድንበራችንን ጥሶ ለመግባት ሙከራ ማድረጉ በእሳት ጨዋታ መሆኑን ሊያውቅ ይባዋል ብለዋል፡፡ለሚቃጣብን ማንኛውም ጥቃት የምንሰጠው የአፀፋ ምላሽ የከፋ መሆኑን አውቆ ቡድኑ አደብ መግዛት አለበት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው […]

ሩሲያ የመጀመሪያውን የኮቪድ19 ክትባት ለዓለም አበረክታለሁ እያለች ነው

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 የሞስኮ ባለ ስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ የኮሮናቫይረስን ክትባት ለመላው ዓለም ለማተዋወቅ ከሁለት ሳምንት ያነሰ ጊዜ ብቻ ነው የቀራቸው፡፡ጋማሊያ ኢንስቲትዩት አገኘሁት ያለውን ክትባት ቢበዛ እስከ ኦገስት 10 ባለው ጊዜ ወስጥ ይፋ አደርጋለሁ ብላለች ሩሲያ፡፡ይሁን እንጂ ሩሲያ ስለ ክትባቱ ሳይንሳዊ ማብራሪያ ከመስጠት መቆጠቧ የውጤታማነቱን ነገር ጥያቄ ውስጥ ይጥለዋል የሚሉ ወገኖች ስጋታቸውን ቀድመው እየገለፁ ነው፡፡ሲ ኤን […]

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በዓሉን ሲያከብር ኮቪድ19 በመከላከል ሊሆን እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 ሙስሊሙ ማህበረሰብ የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓልን ሲያከብር በእምነቱ የተቀመጡ የወረርሽኝ መከላከያ መንገዶችን እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቀመጡ ክልከላዎችን ተግባራዊ በማድረግ መሆን እንዳለበት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እንድሪስ በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡በመግለጫቸውም ሙስሊሙ ማህበረሰብም ይሁን ሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ኮሮናን በመከላከል ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።የዘንድሮውን የአረፋ በዓል የምናከብረው […]

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የጣና ሃይቅን ለመታደግ በህብረት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 በአማራ ክልል የሚገኙ 10ሩም ዩንቨርስቲዎች የጣናን ሃይቅ ለመታደግ በርካታ የምርምር እና የጥናት ስራዎችን መስራታቸውን ለአርትስ ቲቪ ገልፀዋል፡፡ዩንቨርስቲዎቹ በማህበረሰብ አገልግሎት ፤ በሰላም ግንባታና በእሴት ግንባታ ላይ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን እየሰሩ መሆናቸውም ነው የገለፁት ፡፡በተለይም በክልሉ የሚገኘውን የጣና ሃይቅ ለመታደግ በርካታ አማራጮች እና ሙከራዎች መደረጋቸውን የወሎ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት እና የአማራ ዩንቨርስቲዎች ሰብሳቢ ዶክተር […]